ኣንተ ፡ ኮ ፡ ያው ፡ ኣንተ ፡ ነህ (Ante Ko Yaw Ante Neh) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 4.jpg


(4)

Talefe Ya Zemen
(Talefe Ya Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

አንተ እኮ ያው አንተው ነህ/2
ሸለቆም ቢሆን ያው አንተው ነህ
ከፍታም ቢሆን ያው አንተው ነህ
አንተ እኮ ያው አንተው ነህ

ጎንበስ ቀና ብዬ ጌታዬን ላክብረው
ያምላኬ ወለታው እጅጉን ብዙ ነው
በጨነቀኝ ጊዜ በጊዜው መጣና
ጏዳዬን አስዋበው እርሱ ደረሰና ጌታዬ መጣና

አምላኬ ክብር ከሆነልኝማ/2
ልሰዋ ምስጋና
እየሱስ ክብር ከሆነልኝማ/2
ልሰዋ ምስጋና

እሱ እኮ ሲመጣ አምላኬ ሲመጣ
ጌታዬ ሲመጣ አባቴ ሲመጣ
ሁሉ መግቢያ አጣ/2
ችግር መግቢያ አጣ/2

አንተ እኮ ያው አንተው ነህ …

ጠላት አይኑ እያየ እኔን ላከበረ
ገና ጨምራለው መቼ ተዘመረ
አሁን የዘምርኩት ገና ምዘምረው
ለእየሱሰ ክብር ይኸ ይሁንለት አሜን ይሁንለት

አምላኬ ክብር ከሆነልኝማ …

እሱ እኮ ሲመጣ …

አንተ እኮ ያው አንተው ነህ …