ዛሬማ (Zariema) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

አሁን ፡ ገና ፡ ገባኝ ፡ ገና ፡ እንዴት ፡ እንዳለፍኩት
ያንን ፡ የጭንቅ ፡ ቀን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ አየሁት
ማስተዋል ፡ አግኝቼም ፡ አይደል ፡ ጥበብን ፡ ተክኜ
እንዲህ ፡ ነው ፡ አልልም ፡ እንደሰው ፡ እራሴን ፡ ታምኜ

ለካስ ፡ ስለረዳኝ ፡ ስላገዘኝ ፡ እንጂ
ያ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x)
ማን ፡ ያስበኝ ፡ ነበር ፡ ማን ፡ ያነሳኝ ፡ ነበር
ከመቅደሱ ፡ ደጅ ፡ ከመቅደሱ ፡ ደጅ (፪x)

ዘልቄ ፡ እንዳልገባ ፡ አልፌ ፡ የሚታይ ፡ ምንም ፡ የለም
ሞገስ ፡ አገኘሁኝ ፡ በአምላኬ ፡ ጸሎቴም ፡ ተሰማልኝ

አዝ፦ ዛሬማ ፡ ቀና ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬማ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ
ዛሬማ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዛሬማ ፡ ከቤቴ ፡ ገብቶ
ዛሬማ ፡ ቀና ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬማ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ
ዛሬማ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ዛሬማ ፡ ከቤቴ ፡ ገብቶ (፪x)

አሁን ፡ ገና ፡ ገባኝ ፡ ገና ፡ እንዴት ፡ እንዳለፍኩት ፡
ያንን ፡ የጭንቅ ፡ ቀን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ አየሁት
ማስተዋል ፡ አግኝቼም ፡ አይደል ፡ ጥበብን ፡ ተክኜ
እንዲህ ፡ ነው ፡ አልልም ፡ እንደሰው ፡ እራሴን ፡ ታምኜ

ለካስ ፡ ስለረዳኝ ፡ ስላገዘኝ ፡ እንጂ
ያ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x)
ማን ፡ ያስበኝ ፡ ነበር ፡ ማን ፡ ያነሳኝ ፡ ነበር
ከመቅደሱ ፡ ደጅ ፡ ከመቅደሱ ፡ ደጅ (፪x)

ሰው ፡ እንዲያይ ፡ ፊት ፡ አይቶ ፡ አይፈርድም ፡ ልብን ፡ ይመረምራል
በጊዜው ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አርጐ ፡ ታሪኬን ፡ ቀይሮታል

አዝ፦ ዛሬማ ፡ ቀና ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬማ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ
ዛሬማ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዛሬማ ፡ ከቤቴ ፡ ገብቶ
ዛሬማ ፡ ቀና ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬማ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ
ዛሬማ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ዛሬማ ፡ ከቤቴ ፡ ገብቶ (፪x)