ይገባዋል (Yegebawal) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ክብሩን ፡ ጥሎ ፡ መጥቶ
ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ኃጢአት ፡ መብቱን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ
የማይገባውን ፡ ዋጋ ፡ ከፈለ

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ንጉሥ
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ
የሞት ፡ መውጊያን ፡ ሰብሮ ፡ ጥሎት ፡ ተነሳ

አዝ፦ ይገባዋል ፡ ታርዷልና
ብዙ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
ድል ፡ ለነሳው ፡ የድል ፡ ዜማ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንዲሰማ (፪x)

ክብር ፡ ዝና ፡ ባለጠግነት
ለታረደው ፡ በግ ፡ ይሁንለት (፬x)

የቀራንዮ ፡ ስቃይ ፡ ያን ፡ ሁሉ ፡ መከራ
መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ሲወጣ ፡ ተራራ
ሲዘባበቱበት ፡ ሁሉም ፡ በተራ

ባህር ፡ ውቅያኖሱን ፡ የፈጠረ ፡ ጌታ
ተጠማሁኝ ፡ አለ ፡ ተሰቅሎ ፡ ጐልጐታ
የአዳምን ፡ ዘር ፡ ሊያድን ፡ ሞትን ፡ ሊገታ

አዝ፦ ይገባዋል ፡ ታርዷልና
ብዙ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
ድል ፡ ለነሳው ፡ የድል ፡ ዜማ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንዲሰማ (፪x)

ክብር ፡ ዝና ፡ ባለጠግነት
ለታረደው ፡ በግ ፡ ይሁንለት (፬x)

[[Category:]]