ተለመነን (Telemenen) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

ተለመነን (፬x)
አምላካችን ፡ ፈጣሪያችንን

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እስኪ ፡ ተለመነን
እንዲሁ ፡ አንለፍ ፡ ክብርህን ፡ አሳየን (፪x)

በጮማና ፡ በስብ ፡ ስጋቸው ፡ ደልቦ
መንፈሳቸው ፡ ግን ፡ ከሳ ፡ ጽድቅን ፡ ተርቦ
የተመኙ ፡ አግኝተው ፡ ምድራዊውን ፡ ተድላ
ሲደሰቱ ፡ አላየንም ፡ ውስጣቸው ፡ ሲሞላ

መች ፡ ሆነና ፡ ሞገስ ፡ መልካም ፡ በለበሰ
ሰማያዊው ፡ ፀጋ ፡ ከላይ ፡ ካልፈሰሰ
እውነትና ፡ ምህረት ፡ የተገለጡለት
እሱ ፡ ነው ፡ ስጦታ ፡ እሱ ፡ ነው ፡ በረከት

አዝ፦ ተለመነን ፡ ኧኸ ፡ ኧኸ ፡ ተለመነን ፡ ኧኸኸን (፪x)

አቤቱ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እስኪ ፡ ተለመነን
እንዲሁ ፡ አንለፍ ፡ ክብርህን ፡ አሳየን (፪x)

ክብርና ፡ ዝናን ፡ በመቃብር ፡ ሊቀር
ኮበለለ ፡ ወገነ ፡ ሰው ፡ ከጨለማ ፡ ጋር
ቃዬል ፡ በአቤል ፡ ላይ ፡ ወንድም ፡ በወንድሙ
ሞትን ፡ ዘራ ፡ በዘሩ ፡ ይከሰዋል ፡ ደሙ

ወይ ፡ ዘመነ ፡ ምህረት ፡ ጻድቅ ፡ መንገድ ፡ ወድቆ
እግዚአብሔርን ፡ መፍራት ፡ ከትውልድ ፡ እርቆ
ኃጥ ፡ ሲለመልም ፡ ፈራጅ ፡ እንደሌለ
ከልካይ ፡ ሆይ ፡ ተነሳ ፡ ብሎ ፡ ይኸው ፡ አለ

አዝ፦ ተለመነን ፡ ኧኸ ፡ ኧኸ ፡ ተለመነን ፡ ኧኸኸን (፪x)

አቤቱ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እስኪ ፡ ተለመነን
እንዲሁ ፡ አንለፍ ፡ ክብርህን ፡ አሳየን (፪x)

ተለመነን ፡ ኧኸ ፡ ኧኸ ፡ ተለመነን ፡ ኧኸኸን (፬x)