ምን ፡ ይለኛል (Men Yelegnal) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

አዝ፦ ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
የሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ሚስጥሩ ፡ ያልገባው (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
እኔስ ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እርቃኔን ፡ ባመልከው (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
ብዬስ ፡ አምልኮዬን ፡ ፈጽሞ ፡ አልቀንስም (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
የሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ዝምም ፡ አያሰኝም (አዎ)

ያለውን ፡ ይበል ፡ እንጂ ፡ ያሻውን ፡ እንደልቡ
ያልገባው ፡ ያልተረዳው ፡ ቢተቸኝ ፡ እንደ ፡ ሃሳቡ
ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ላነሳኝ ፡ ለክብሩ ፡ እዘምራለሁ
ከውርደቴ ፡ ላሰበኝ ፡ ለስሙ ፡ እቀኛለሁ
(፪x)

የምስኪን ፡ ወዳጅ ፡ ለድሃደጉ
አባት ፡ ለሌለው ፡ ክብሩ ፡ ማዕረጉ
ያየ ፡ ይመስክር ፡ የማይረሳት ፡ ሰው
ያለፍኩበትን ፡ እኔስ ፡ አልረሳው

ውለታውን ፡ እስኪ ፡ ላነሳሳው ፡ እንዴት ፡ ልርሳው (፬x)

እንዴት ፡ እንደረዳኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው (፪x)

ውለታውን ፡ እስኪ ፡ ላነሳሳው ፡ እንዴት ፡ ልርሳው (፪x)

ፍቅሩን ፡ ምህረቱን ፡ ቀምሼዋለሁ
እንደ ፡ ኢየሱሴማ ፡ የት ፡ አገኛለሁ
እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ለእርሱ ፡ ብዘምር
አልጨርሰውም ፡ ሁሉን ፡ ብናገር

ውለታውን ፡ እስኪ ፡ ላነሳሳው ፡ እንዴት ፡ ልርሳው (፬x)

አዝ፦ ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
የሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ሚስጥሩ ፡ ያልገባው (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
እኔስ ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እርቃኔን ፡ ባመልከው (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
ብዬስ ፡ አምልኮዬን ፡ ፈጽሞ ፡ አልቀንስም (አዎ)
ምን ፡ ይለኛል ፡ (ምን ፡ ይለኛል)
የሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ዝምም ፡ አያሰኝም (አዎ)

ያለውን ፡ ይበል ፡ እንጂ ፡ ያሻውን ፡ እንደልቡ
ያልገባው ፡ ያልተረዳው ፡ ቢተቸኝ ፡ እንደ ፡ ሃሳቡ
ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ላነሳኝ ፡ ለክብሩ ፡ እዘምራለሁ
ከውርደቴ ፡ ላሰበኝ ፡ ለስሙ ፡ እቀኛለሁ
(፪x)