ማረን (Maren) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

አዝ፦ ማረና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረና
ማረና ፡ አሁንም ፡ ማረና
ማረና ፡ አመጻችን ፡ በዝቶን
ማረና ፡ ደካክመናልና (፪x)

ሳናውቅ ፡ በስህተት ፡ ከሰራነው ፡ ይልቅ
የድፍረት ፡ ኃጢአታችን ፡ በዛ
አሁንስ ፡ ፈርተናል ፡ እጅግ ፡ ተጨንቀናል
በፊትህ ፡ ለመቆም ፡ አቅም ፡ የለንምና

ማረና

አዝ፦ ማረና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረና
ማረና ፡ አሁንም ፡ ማረና
ማረና ፡ አመጻችን ፡ በዝቶን
ማረና ፡ ደካክመናልና (፪x)

የቆምን ፡ ሲመስለን ፡ ያለንበት ፡ ከፍታ
በኃጢአት ፡ ተጠምደን ፡ ታስረን ፡ ሳንፈታ
በሰው ፡ ፊት ፡ ሙሉ ፡ ነን ፡ አልጐደለብንም
ጓዳችን ፡ ሲፈተሽ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ የለንም

ማረና

አዝ፦ ማረና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረና
ማረና ፡ አሁንም ፡ ማረና
ማረና ፡ አመጻችን ፡ በዝቶን
ማረና ፡ ደካክመናልና (፪x)

እስኪ ፡ ማረን ፡ ተቀበለን
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ማንም ፡ የለን
አባ ፡ ማረን ፡ ተቀበለን
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ማንም ፡ የለን (፭x)

አዝ፦ ማረና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረና
ማረና ፡ አሁንም ፡ ማረና
ማረና ፡ አመጻችን ፡ በዝቶን
ማረና ፡ ደካክመናልና (፪x)