አይጥልም (Aytelem) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin & Teddy)

Mesfin & Teddy Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin & Teddy)

ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ትውስ ፡ ይለኛል
ለኔ ፡ ያደረግከው ፡ ከቶ ፡ አልረሳው

የማልችለውን ፡ እያስቻለኝ ፡ አቤት ፡ ስንቱን ፡ ቀን ፡ አሳለፈኝ
ተራራው ፡ ሸለቆው ፡ እንዳያደክመኝ ፡ በአባትነት ፡ ቃሉ ፡ እያባበለኝ
እያጽናናኝ ፡ (አሄሄሄ) ፡ በቤቱ ፡ አኖረኝ
(፪x)

አዝ፦ አይጥልም ፡ አይረሳም ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሲያኖረኝ ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ (አሄ) (፪x)

ትዝ ፡ እያለኝ ፡ ትውስ ፡ እያለኝ
ያ ፡ ሁሉ ፡ መከራ ፡ በላዬ ፡ ያለፈ ፡ እስካይምስለኝ ፡ እንባዬ
እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ አለፈ ፡ ሃዘኔ ፡ ከኔ ፡ ተገፈፈ

እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ አለፈ ፡ (እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ አለፈ) (፬x)
እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ አለፈ ፡ (ሃዘኔ ፡ ከኔ ፡ ተገፈፈ) (፪x)
እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ መከራዬ ፡ አለፈ (፪x)
አለፈና ፡ አለፈና

ያልተፈጠሩት ፡ ቀናቶቼን ፡ ቀድሞ ፡ ሲያቀናልኝ ፡ መንገዴን
የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ እጣ ፡ ፈንታዬ ፡ እንደዘመርኩለት ፡ ሆኖኝ ፡ ካሳዬ
ተጽናናሁኝ ፡ (አሄሄሄ) ፡ ታብሶ ፡ ዕንባዬ
(፪x)

አዝ፦ አይጥልም ፡ አይረሳም ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሲያኖረኝ ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ (አሄ) (፪x)