ማረፊያዬ ፡ ነህ (Marefiayie Neh) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንዲሁ ፡ በዋዛ
(Endihu Bewaza)

ዓ.ም. (Year): (2005)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

አዝማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ያረፍኩብህ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ የተመካሁብህ
(፪x)
ማምለጫዬ ፡ ነህ ፡ ያመለጥኩብህ
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ ማምለጫ (፫x)
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ አንተ ፡ ብቻ

ማረፊያዬ ፡ ጌታዬ
መመኪያዬ ፡ ጌታዬ
ነው ፡ ሰላሜ ፡ ጌታዬ (፪x)

ጉልበት ፡ ሆኖ ፡ እያበረታ
ያንን ፡ ዘመን ፡ በእርሱ ፡ አለፍኩኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅሩ
ለደካማው ፡ ሲሰጥ ፡ ብርታቱ

ታሪኬን ፡ ቀየረው ፡ ቀያየረው
ኑሮዬን ፡ ለወጠው ፡ አጣፈጠው
ብሰግድለት ፡ ለእርሱ ፡ ሲያንስበት ፡ ነው (፫x)

አዝማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ያረፍኩብህ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ የተመካሁብህ
(፪x)
ማምለጫዬ ፡ ነህ ፡ ያመለጥኩብህ
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ ማምለጫ (፫x)
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ አንተ ፡ ብቻ

ረግቻለው ፡ እኔስ ፡ በአምላኬ
እኖራለሁ ፡ ተደላድዬ
መጨነቄን ፡ ከላዬ ፡ ወስዶ
አሳረፈኝ ፡ ሰላሙን ፡ ሰጥቶ

ታሪኬን ፡ ቀየረው ፡ ቀያየረው
ኑሮዬን ፡ ለወጠው ፡ አጣፈጠው
ብሰግድለት ፡ ለእርሱ ፡ ሲያንስበት ፡ ነው (፫x)

አዝማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ያረፍኩብህ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ የተመካሁብህ
(፪x)
ማምለጫዬ ፡ ነህ ፡ ያመለጥኩብህ
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ ማምለጫ (፫x)
ማምለጫ ፡ ማምለጫ ፡ አንተ ፡ ብቻ

ማረፊያዬ ፡ ጌታዬ
መመኪያዬ ፡ ጌታዬ
ነው ፡ ሰላሜ ፡ ጌታዬ (፪x)