From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ልዑልን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ
ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x)
ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ
ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x)
ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው (፫x)
እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው
እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x)
እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x)
እንደተናገርው ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው ፣ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (፪x)
አይመስለኝም ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ የሚፈጸም
ኑሮዬን ፡ ሕይወቴን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው
ይህ ፡ ሁሉ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ ያለው ፡ ግን ፡ ይሆናል
እርሱ ፡ መች ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ተናግሮ ፡ ዝም ፡ ይላል
ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x)
ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x)
ልዑልን/ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ
ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x)
ተናግሮ ፡ ማድረግን ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል
ታዲያ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ብሎሃል
ጠብቀው ፡ ተስፋህን ፡ አትወላውል ፡ ጽና
የተናገረህን ፡ ሲፈፅም ፡ እንድታይ
ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x)
ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x)
ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው (፫x)
እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው (፫x)
እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x)
እንደተናገርው ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው ፣ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (፪x)
ተናግሮ ፡ ማድረግን ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል
ታዲያ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ብሎሻል
ጠብቂው ፡ ተስፋህን ፡ አትወላውይ ፡ ጽኚ
የተናገረሽን ፡ ሲፈፅም ፡ እንድታዪ
ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x)
ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x)
ልዑልን/ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ
ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x)
|