From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ከመወለዴ ፡ ጀምሮ ፡ የማውቀው ፡ መልካም ፡ አንድ ፡ ነው
ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ የማውቀው ፡ መልካም ፡ አንድ ፡ ነው
እርሱም ፡ አንተን ፡ ነው (፫x)
ጌታ ፡ መልካም ፡ ነው
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሥልጣንህ ፡ ገደብ ፡ የለው
ኢየሱስ ፡ መንግሥትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው
በዙፋንህ ፡ ፀንተህ ፡ ጥንትም ፡ ነበርክ
ዛሬም ፡ በክብር ፡ አለህ
ለዘለዓለም ፡ ደግሞ ፡ በሥልጣንህ
ገና ፡ ትኖራለህ
ከሁሉም በላይ ነህ የኔ ጌታ፣
ሁሉን ትገዛለህ
የሚወዳደርህ አቻ የለህ፣
አንተ እጅግ ታላቅ ነህ
አምላኬ አምላኬ እንዳንተ …..
ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ በጆሮዬ :ጌታ ማዳንህን
ለብዙዎች ፡ ጥላ ፡ የማምለጫ ፡ አለት ፡ መሆንህን
በእውነትም ፡ አዳኝ ፡ ነህ ፡ መድሃኒቴ እኔም ፡ አይቻለሁ ፡
ከዚህ ፡ ከጨለማ ከሞት ፡ መንደር ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ
ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ጆሮዬም አልሰማም፣
ጌታ እንዳንተ መልካም፣ አይኖቼም አላዩም፣
ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ከቶ አልገጠመኝም፣
ለዘላለም ክበር፣ ከፍ በልልኝ(፪x)
እንዳንተ የሚሆን ለኔ የለም፣
አንተ ልዩ ከሁሉ ከላይ ነህ፣
አልፋና ኦሜጋ የኔ ጌታ፣
ዘላለም በክብር ምትበረታ
አልፋና ኦሜጋ አቻ የለህ
ዘላለም በክብር ትኖራለህ
ከመወለዴ ፡ ጀምሮ ….
|