From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)
ለእኔስ ፡ የሆነዉ
የሆነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነዉ ፡ የሆነዉ
ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሆዪ
ለእኔስ ፡ ያደረከውን ፡ ነገር ፡ ሳስበው (፬x)
ቆጥሬ ፡ አልዘልቀው (፪x)
በኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ አቤት ፡ የሚያስገርመው
ከሞት ፡ ከጥፋት ፡ ነጥቆ ፡ አኖረኝ ፡ ሕይወት ፡ ሰጥቶ
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላክብረው ፡ ይህን ፡ ጌታ
መልካሙን ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ለሆነልኝ ፡ መድሃኒቴ (፪x)
አዝ፦ ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)
ለእኔስ ፡ የሆነዉ
የሆነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነዉ ፡ የሆነዉ
ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነዉ ፡ ለእኔስ ፡ የሆነዉ (፬x)
ተቅበዝባዥ ፡ እረፍት ፡ ያጣሁ ፡ አሁን ፡ ግን ፡ በአንተ ፡ ረጋሁ
በሰላም ፡ መውጣት ፡ መግባት ፡ ሆነልኝ ፡ በዝቶ ፡ ምህረት
በለምለም ፡ መስክ ፡ ለመራኝ ፡ ከመንፈሱን ፡ ላጠጣኝ
መልካሙን ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝ ፡ ጌታዬ/ኢየሱሴ ፡ እንካ ፡ ተቀበለኝ(፪x)
አዝ፦ ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)
ለእኔስ ፡ የሆነዉ
የሆነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነዉ ፡ የሆነዉ
ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
ሁሉም ፡ በእርሱ ፡ ነዉ ፡ ለእኔስ ፡ የሆነዉ (፬x)
|