From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አበቃ ፡ አከተመ ፡ በተባለ ፡ ጊዜ
ማነው ፡ ለእኔስ ፡ ፈጥኖ ፡ የደረሰው (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አሃ (፫x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ይህን ፡ ያደረገው
እስራቴን ፡ ፈተህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብረህ
ያስጨነቀኝ ፡ ጠላት ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ ጥለህ
ዛሬማ ፡ ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ይኸው ፡ በኢየሱስ
ዘለዓለም ፡ ልገዛ ፡ ልስገድልህ (፪x)
አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ረዳት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
አባት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ረዳት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ሲረዳኝ ፡ በዓይኔ ፡ እያየሁ
ሲያግዘኝ ፡ በዓይኔ ፡ እያየሁ (፪x)
ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ ሁሉን ፡ አለፍኩ
መቼ ፡ አንተን ፡ ይዤ ፡ እኔስ ፡ አፈርኩ
ዛሬም ፡ የሚያቅተኝ ፡ ሁሉ
እወጣዋለሁ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ኃይሉ (፪x)
አበቃ ፡ አከተመ ፡ በተባለ ፡ ጊዜ
ማነው ፡ ለእኔስ ፡ ፈጥኖ ፡ የደረሰው (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አሃ (፫x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ይህን ፡ ያደረገው
አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ረዳት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
አባት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ረዳት ፡ እንደሌለው ፡ ለምን ፡ አዝናለሁ
ሲረዳኝ ፡ በዓይኔ ፡ እያየሁ
ሲያግዘኝ ፡ በዓይኔ ፡ እያየሁ (፪x)
|