እልልታ (Elilta) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

Linurilih
(Linurilih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2023)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ለማጉረምረም አልከፍትም አንደበቴን አንደበቴን
ቀድሼ አቀርባለሁ ሰውነቴን ሰውነቴን/2

ሲነገር የህይወቴ ምስክርነት
ተጨመቆ የሚገልፀው ነው አንድ ነገር

እልልታ እልልታ እልልታ ለደጉ ጌታ
እልልታ እልልታ እልልታ ለህይወቴ ጅግና

ይሰማል እልልታ በቤተ በጏዳ
ከመላእክቶች ጋራ ሲሰዋ ለጌታ በለሊት በማለዳ
ይሰዋል አምልኮ ሰማይን ሰንጥቆ
ሲዋላው ጎጆዬን የጥንቱ ምስጋና ሲደረደር ለጌታ

እኔም አነሳሁ በገናዬን ተቀላቅዬ የቅዱሳንን ጉባኤ
አለኝ ምሰዋው የምሰጠው በልቤ ሞልቶ የሚፈሰው

እልልታ እልልታ እልልታ ለደጉ ጌታ
እልልታ እልልታ እልልታ ለህይወቴ ጅግና

የተደረገልኝ ተአምር በህይወቴ በህይወቴ
ያስነጠከኝ ያዳንከኝ ከልጅነቴ ከልጅነቴ/2

እንኳን ዝም ልል ልታዘብ እንዳልሆነለት
ጨርቄን አስጥሎኝ ምህረትህ ውላለሁ ሳመልክ

በእልልታ በእልልታ በእልልታ ላምልክህ ጌታ
እልልታ እልልታ እልልታ ለህይወቴ ጀግና
እልልታ እልልታ እልልታ ለደጉ ጌታ
እልልታ እልልታ እልልታ ለህይወቴ ጅግና

የእኔና ቤተ እልልታ የዘር ማንዘሬ እልልታ
ከልብ የሆነው እልልታ ይድረሽ የኔ ጌታ
የእኔና ቤተ እልልታ የዘር ሃረጌ እልልታ
ከልብ የሆነው እልልታ ይድረሽ የኔ ጌታ

እልልታ እልልታ እልልታ ለደጉ ጌታ
እልልታ እልልታ እልልታ ለህይወቴ ጅግና