From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ወደ ቤተል መጀመርያ ወዳወቁህ ስፍራ እመለሳለሁ
ቃል ኪዳኔን አድሳለሁ
ህያውን መስዋዕት ሰውነቴን በፊትህ አቀርባለሁ
ከእንግዲ መኖርያዬ እዚሁ ነው በቤተል ነው
ከእንግዲ ማደርያዬ እዚህ ነው በልፍኝህ ነው
መሰውያዬ ዘላለም በፊትህ እሳት ይኑረው
ያርግ ወደማደሪያህ እጣኑን አሽትተው
ደስ ያሰኝህ ልብህን ያርካው መቅደስህን ይሙላው/2
ሰውነቴ ድኖ ቀረ አልለቅ ህም ብዬ የባረከኝ ለታ
ቅብዝብህ ነፍሴ በእጅህ ተዳሳ/2
በጥልቁ ፍቅርህ ለአንዴና ለመጨረሻ ተማርካ
ዘወትር ትጠብቃለች አንተን ተርባ
በየለት ትጠራሃለች አንተን ተርባ
ዘወትር ትጠብቃለች አንተን ተርባ
በየለት ትጠራሃለች አንተን ተርባ
መሰውያዬ ዘላለም በፊትህ እሳት ይኑረው
ያርግ ወደማደሪያህ እጣኑን አሽትተው
ደስ ያሰኝህ ልብህን ያርካው መቅደስህን ይሙላው/2
እኔና ቤቴ ዘር ማንዘሬ ልንከተልህ ልንገዛልህ
እንቀድሳለን ማዳሪያችንን ለንጉሳችን
አንተን ሚመጥን ልብህን ሚያረካ የሚያስደስትህ
ይሁንልህ ሁለንተናችን ይሁንልህ ስውርጏዳችን
ሁሉ ባንተ ላንተ ካንተ ነው/6
|