ስለምወድህ (Silmwedih) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

Silmwedih
(Silmwedih)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 8:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ኦ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ
እየሱስ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ

ከቃላት ያለፈ ፍቅር
ዋጋን የሚያስከፍል መሰዋት
ይዤልህ ልምጣ እንደገና
ብቸኛውን ይሳቄን ልሰዋ

እራስህን በቃልኪዳንህ የሰጠኸኝ እንኳን
አይበልጥብኝም ካንተ እራስህ
አይተካልኝም አብሮነትህን

አልሸሽግም የልቤን ክፍሎች ወደሗላ
አልደብቅም በሬ ክፍት ነው ላንተ ጌታ
መርምረኝ የውስጠኛዬን ጠልቀህ እወቀው
ታደገኝ ብኩርናዬን እንዳልሸጠው
በመታዘዜ እንድወድህ
እድሜ ዘመኔን እንድገዛልህ

ኦ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ
እየሱስ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ

መሰዋቴን ላዘጋጅልህ እንዳዘዝከኝ
ቢሸከምም የተስፈዬን ቃሌ ራስህ የሰጠኸኝ
አልቆጥረውም የምድረኛውን ዋና አድርጌ
ርስቴ አንተው ነህ ሌላው አይጎድለኝ ቢወጣ ከእጄ

ብቻ ጌታዬ ደስ ይበልህ ሁለንተናዬ ያገልግልህ
ብቻ ጌታዬ ደስ ይበልህ ሁለንተናዬ ያገልግልህ

ኦ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ
እየሱስ ወዴ ስለምወድህ ስለምወድህ ሁለንተናዬ የኸውልህ

ከቃላት ያለፈ ፍቅር
ዋጋን የሚያስከፍል መሰዋት
ይዤልህ ልምጣ እንደገና
ብቸኛውን ይሳቄን ልሰዋ