ፍለጋ (Filega) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

Silemwedih
(Silemwedih)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ቆይቼ ልጥና ደጅህን
ደጋግሜ ላንኳኳ በርህን
የመንፈስህ ነኝ እረሃብተኛ
ሰርተኸኝ በሌላ እንዳልረካ

ይሄን አውቄ ነፍሴ ተሸኝፋ
እጅ ሰታለች እስከዘላለሟ

ብትወድ በሃይለኛው ንፋስህ
ብትወድ በነበልባል እሳት
ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታ
ብትወድ በትንሿ ኮሽታ

ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና
አንተ ብቻ ና አንተ ብቻ ና

አስቀድሜ ፅድቅህን አስቀድሜ ፊትህን
አስቀድሜ ወደጏዳ አስቀድሜ በሬን ልዝጋ
መጀመሪያ ፅድቅህን መጀመሪያ ፊትህን
መጀመሪያ ወደጏዳ መጀመሪያ ላወጋህ

ፍለጋ ፍለጋ ፍለጋ
ቀኖቼ ይለቁ አንተን ፍለጋ

ይሰበር አልባስጥሮሴ
ከእግርህ ስር ሙሉ ማንነቴ
ይጠበው እግርህን እንባዬ
እንደ ውሃ ፊትህ ይፍሰስ ነፍሴ

ካንተ ውጪ እኔነ የለኝም
መሰዊያው ላይ ህኸው አለሁኝ

ብትወድ በሃይለኛው ንፋስህ
ብትወድ በነበልባል እሳት
ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታ
ብትወድ በትንሿ ኮሽታ

ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና
አንተ ብቻ ና አንተ ብቻ ና

አልሰለችም አንተን መጠበቅ ቀንና ለሊት
አይደክመኝም እጠብቅሃለሁ ቀንና ለሊት
የዘላለም ረሃቤ ነህ የዘላለም እርካታዬ
አያረካኸኝ ምራብህ እየሞላኸኝ ምጠማህ
ከጎኔ ሆነህ ምናፍቅህ እየዳሰስከኝ ምራብህ
ከጎኔ ሆነህ ምናፍቅህ እየዳሰስከኝ ምራብህ

አተረፍኩ አንተን አንተን ስላልኩ አንተረፍኩ
አወኩበት አንተን ስለመረጥኩ አወኩበት
አተረፍኩ ክብሬ ስላረኩን አተረፍኩ
አወኩበት አንተን ስለወደድኩ አወኩበት

አስቀድሜ ፅድቅህን አስቀድሜ ፊትህን
አስቀድሜ ወደጏዳ አስቀድሜ በሬን ልዝጋ
መጀመሪያ ፅድቅህን መጀመሪያ ፊትህን
መጀመሪያ ወደጏዳ መጀመሪያ ላወጋህ

ፍለጋ ፍለጋ ፍለጋ
ቀኖቼ ይለቁ አንተን ፍለጋ