From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
እሮጥኩኝ ፡ እሮጥኩኝ ፡ ለብዙ ፡ ዘመን
ፍቅርን ፡ የማገኘው ፡ በልፋት ፡ መስሎኝ
ዝም ፡ አልከኝ ፡ እስክመጣ ፡ ድክሞኝ ፡ በቅቶኝ
እጄን ፡ እስክሰጥህ ፡ መፍትሄ ፡ ጠፍቶኝ
ታገስከኝ ፡ ልትለኝ
እኔ ፡ ነኝ ፡ የማነጻሽ ፡ ወደሃሳቤ ፡ ምመልስሽ
እኔ ፡ ነኝ ፡ የመረጥኩሽ ፡ ወደ ፡ እራሴ ፡ የምስብሽ
እኔ ፡ ነኝ ፡ የምለይሽ ፡ በፍቃዴ ፡ የማስኬድሽ
ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
ሃሳቤን ፡ በሙሉ ፡ ከሩቅ ፡ ታውቀዋለህ
የሥጋዬን ፡ ድክመት ፡ አዎ ፡ ታየዋለህ
የለኝም ፡ ማቀርበው ፡ ከእኔ ፡ የሆነ
በቅድስና ፡ ውስጥ ፡ ለመቆም ፡ የቻለ
ግን ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ሚያስገባኝ ፡ ወደ ፡ አንተ
ሊቀ ፡ ካህን ፡ ለዘለዓለም
የሚሽረው ፡ አንዳችም ፡ የለም X፪
በአንተ ፡ ፊት ፡ ሚማልድልኝ
እንዳልጠፋ ፡ የሚዋጋልኝ
ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
በጨለማ ፡ ብሆን ፡ አንተ ፡ ብርሃኔ ፡ ነህ
መንገዴንም ፡ ብስት ፡ ትመልሰኛለህ
አልፈቀድክለትም ፡ ከሳሼ ፡ እንዲቀጥል
ቀደህ ፡ እስክታስወግድ ፡ የጥፋቴን ፡ ዝርዝር
ከፍለህ ፡ ዋጋዬ ፡ የሃጥያት ፡ እዳዬን
አስታረከኝ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ
በሰራኸው ፡ የመስቀል ፡ ስራ X፪
ወደኸኛል ፡ ገና ፡ ሳላውቅህ
ይደንቀኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ
ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል
እኔስ ፡ ይደንቀኛል
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪
ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ
በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
|