ፍፁም ፡ ነህ (Fetsum Neh) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ
ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ

ወደ ፡ ምድረበዳ ፡ አባብላታለሁ
ሚስጥሬን ፡ ለመግለጽ ፡ እኔ ፡ እለያታለሁ
ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ ለበጐ ፡ ነው
ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ በፍቅርህ ፡ ነው
ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ ወደኽኝ ፡ ነው
ስለኔ ፡ ያረግከው ፡ ለካ ፡ መርጠኽኝ ፡ ነው

ጥያቄ ፡ የለኝም ፡ መልስ ፡ አንተ ፡ ሆነኸኝ
በማ እ፡ በሉ ፡ ምርሃል ፡ መኖር ፡ አስለመድኸኝ
ቢያይልም ፡ ወጀቡ ፡ ቢቆጣም ፡ ነፋሱ
ይታዘዛል ፡ ሁሉም ፡ ለአንተ ፡ ለንጉሡ

ለእኔስ ፡ ሆኖልኛል ፡ ሃይልህን ፡ የማይበት
የጠላቴ ፡ ወጥመድ ፡ ራሱ ፡ ሚያዝበት
አብረኸኝ ፡ እስከ ፡ ሆንክ ፡ በመርከበ ፡ ላይ
ለመልካም ፡ ይሆናል ፡ ክብርህን ፡ እማይበት

አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ
ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ

በዓይኖቸ ፡ ማየው ፡ በፊቴ ፡ ያለው
እያንዳንዱን ፡ ነገር ፡ ፈቅደህለት ፡ ነው
በዙፋንህ ፡ ሆነህ ፡ ትመለከታለህ
ግድ ፡ ይለኛል ፡ ለኔ ፡ ልጄ ፡ ነች ፡ ትላለህ
እኔ ፡ ባይገባኝም ፡ ማልፈውን ፡ ጐዳና
የምሕረት ፡ እጆችህ ፡ አቅፈውኛልና
ዛሬም ፡ አምንሃለሁ ፡ አዎ ፡ እንደገና
ነፍሴ ፡ አረጋግጣለች ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ጌታ
አትተወኝም ፡ ጌታ

አንተን ፡ ለሚወዱ ፡ በአንተ ፡ ለተጠሩ
ለበጐ ፡ ይሆናል ፡ የሚያልፉበት ፡ ሁሉ
አትደክም ፡ አትተኛ ፡ አትዝል ፡ አትረሳ
ታውቀሃል ፡ እንደሆንክ ፡ መልካሙ ፡ እረኛ
በበትህ ፡ የኖረ ፡ በአንተ ፡ የተመካ
አያፍርም ፡ ዘለዓለም ፡ ለአንድም ፡ ደቂቃ
ግን ፡ አስቀምጠኸው ፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ በከፍታ
ከሞገስህ ፡ ጠግቦ ፡ ይኖራል ፡ በግርማ

አዝ፦ ፍፁም ፡ ነህ ፡ ፍፁም ፡ በአደራረግህ
ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጻድቅ ፡ በአሰራርህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ በአደራረግህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ በአሰራርህ