ፍቅር ፡ ማለት (Feqer Malet) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

አልሳሳ ፡ በልጅህ ፡ ሲመጣ
አልቀስ ፡ የቁጣህን ፡ መጠን
እኔ ፡ ላጠፋሁት ፡ ክፉ ፡ ላደረኩት
ሰዋኸው ፡ ቅዱሱን ፡ ሃጥያት ፡ ያላየውን
የዓለም ፡ ፍርድን ፡ ሲወስድ
ፊትህን ፡ ያዞርከው
አስበኸኝ ፡ ነው ፡ ወደኸኝ ፡ ነው
መርጠኸኝ ፡ ነው ፡ አውቀኸኝ ፡ ነው
ራርተህልኝ ፡ ነው ፡ አዝነህልኝ ፡ ነው
ሳስተህልኝ ፡ ነው ፡ አፍቅረኸኝ ፡ ነው

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ

ደግ ፡ ነህ ፡ ክፉ ፡ ላሰበብህ
ትራራለህ ፡ ልቡን ፡ ላዞረብህ
እየዘበቱብህ ፡ እያሾፉብህ
ስራቸውን ፡ አያውቁም ፡ የሚያደርጉትን
ምሕረት ፡ አርግላቸው ፡ ብለህ ፡ የጸለይክ
ልዩ ፡ ነህ ፡ የተለየህ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ አቤት ፡ ምሕረትህ
ውብ ፡ ነህ ፡ የተለየህ
አቤት ፡ በጐነትህ ፡ አቤቱ ፡ ፍቅርህ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ

ምሕረትህ ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ
አዲስ ፡ ነው ፡ በየጥዋቱ
ሃጥያትን ፡ ለሰሩ ፡ ለበደሉ
እጅህ ፡ ይዘረጋል ፡ ለያንዳንዱ
የትላንቱን ፡ እረስተህ ፡ እንዳጠፉ
ምሕረትህ ፡ ብዙ ፡ በጐነትህ ፡ ብዙ
ፍቅርህ ፡ ብዙ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዙ
ትህትናህ ፡ ብዙ ፡ ርህራሄህ ፡ ብዙ
ትዕግሥትህ ፡ ብዙ ፡ መውደድህ ፡ ብዙ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ አንተ ፡ ነሀ
ሲጀመርም ፡ ሲጨረስ
ብቻህን ፡ ፍቅር ፡ ነህ