እጠብቃለሁ (Etebeqalehu) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

እጠብቅሀለው ባስቀመጥከኝ ቦታ
እጠብቅሀለው አትዘገይምና
እጠብቅሀለው ባስቀመጥከኝ ስፍራ
እጠብቅሀለው አትዘገይምና

በኔ ፈቃድ ባይሆን ባሰብኩት መንገድ
እንደማትጥለኝ አልጠራጠርም
ታማኝ ነህ ተስፋን የሰጠኸኝ
ታማኝ ነህ አኖርሻለው ያልከኝ
ታማኝ ነህ ተስፋን የሰጠኸኝ
ታማኝ ነህ አቆምሻለውአኖርሻለው ያልከኝ

ዘመናት አለፉ አመታት ወራት
የታለ እያሉ አምላክ አባትሽ
ባክሽ እረስቶሻል ተይው ነገሩን
ብታምኚ ይሻላል የእጅ ስራሽን
እኔስ አምነዋለው ባያድነኝ እንኳን
ብሞትም ይችላል ሊያወጣኝ ከሙታን

ደመናም አላይም ሸለቆ ይሞላል
ንፋስም አላይም ሸለቆ ይሞላል
ዝናብም አላይም ሸለቆ ይሞላል
አምላኬ አዞታል አባቴ አዞታል