From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ያስፈልገኛል ያልኩትን ዞር ብዬ ተመልክቼ
ካንተ ሚለዩኝን ነገሮች ዞር ብዬ ተመልክቼ
ምንኛ ታልዬ ነበር ህይወትን የፈለኩት
በሙታን መንደር በሌለህበት
በሙታን መንደር ባልነገስክበት
በሙታን መንደር በሌለህበት
በሙታን መንደር ባልከበርክበት
አሁንማ አሁንማ ውስጤ የለም ባዶ ቦታ
አሁንማ አሁንማ ከብረህበት የኔ ጌታ
አሁንማ አሁንማ ውስጤ የለም ባዶ ስፍራ
አሁንማ አሁንማ ነግሰህበት የኔ ጌታ
ጥያቄ የለኝም ምኞቴን አንድ ነው
ዘመኔ እንድታልፍ ፊትህን እያየው ክብርህን እያየው
ግርማህን እያየው ውበትህን እያየሁ/2
እግዚአብሔች ያለው ሁሉም አለው
እግዚአብሔች ያለው ምንም አልቀረው
ሰማያትን የዘረጋው ያከበረው
ኧረ ምን ቀረው ኧረ ምን ቀረው
እየሱስ ያለው ሁሉም አለው
እየሱስ ያለው ምንም አልቀረው
ሰማያትን የፈጠረው የወደደው
ኧረ ምን ቀረው ኧረ ምን ቀረው
አንተ በፈቀድከው መንገድ መሄድን ተስማምቼ
አንተ በወደድከው መንገድ መሄድን ተስማምቼ
ምንኛ ሰላም አገኘው ለነፍሴም እረፍት
ከክብር ወደ ክብር አሻግረኸኝ/2
ክግርማ ወድ ግርማ አሻግረኸኝ/2
አሁንማ አሁንማ ለኔ የለም ሌላ ምርጫ
አሁንማ አሁንማ መንገዴ ነህ አንተ ብቻ/2
ጥያቄ የለኝም ምኞቴን …
እግዚአብሔች ያለው …
ከተመስገን ሌላ ቃል አለ ውይ ላንተ ሚሆን
ከተባረክ ሌላ ቃል አለ ውይ ላንተ ምሰጥህ
ህይወቴን በፍቅርህ ሞልተኸዋልና
ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምስጋና
ዘመኔን በቃልህ አስውበሃልና
ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምስጋና
|