አስረሳኝ (Asresagn) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

አስረሳኝ የድሮውን አስረሳኝ የባከነውን
ዘመናት እንባዬን የፈሰውን
አስረሳኝ እንዳልነበረ
አሳቀኝ ህይወቴን ቀየረ/2

ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው
እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2

ያጠፋሁት ዘመን ስጋዬን ታምኜ
የጠቀመኝ መስሎኝ እጅጉን ታልዬ
እንዲሁ ስባክን መሰዊያዬን ትቼ
ምህረትህ አገኘኝ ባዶዬን ቀርቼ
መጣሁ እጄን ሰጥቼ

አለቀ አበቃ ባልኩበት በሃር ላይ
በሃይልህ ተገለጥክ የእኔ ተበቃይ
ህይወትን ልትዘራ በሞተው ነገር ላይ
አላስቻለህ ልብህ የእኔን እንባ ስታይ
ወደድክ ልትመጣ ከላይ

ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው
እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2

የምርጦቹ ምርጦች ቢሰበሰቡለት
እውቀት የተካቡት ቢመሰክሩለት
እንኯን ሊመጥነው ፈፅሞም አይገልፀው
ታዲያ እኔ ምንድን ነኝ ባይኑ የምታየው
ይሄስ እውነት ፍቅር ነው

አስረሳኝ የድሮውን አስረሳኝ የባከነውን
ዘመናት እንባዬን የፈሰውን
አስረሳኝ እንዳልነበረ
አሳቀኝ ህይወቴን ቀየረ/2

ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው
እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2