አምንሃለሁ (Amnehalehu) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይገባኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይሞላም ፡ በእጄ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይመስለኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
እኔ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እጄ ፡ ባለው
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የታዘዘውን
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የተላከውን

ይታለፋል ፡ ይታለፋል ፡ ነገር ፡ ሁሉ
እንዳልነበር ፡ እንዳልሆነ ፡ በቀላሉ
ባንተ ፡ ብርታት ፡ ባንተ ፡ ጉልበት ፡ ለተመኩ
መንገድ ፡ አለ ፡ መውጫ ፡ አለ ፡ ከወጥመዱ
አይቻለው ፡ አጥንቶቼን ፡ ስታበረታ ፡
በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ህይወትን ፡ ስትዘራ
ለፃድቅ ፡ ነህ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መጠለያ
የፀና ፡ ግንብ ፡ ላመኑብህ ፡ ኦ ፡ መከታ

አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይገባኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይሞላም ፡ በእጄ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይመስለኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
እኔ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እጄ ፡ ባለው
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የታዘዘውን
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የተላከውን

አንተ ፡ አይደለህ ፡ በዘመናት ፡ የታወከው
በመልካምነትህ ፡ ህዝቡን ፡ ፀጥ ፡ ያረከው
ባይመሰክር ፡ አፉን ፡ ከፍቶ ፡ ስጋ ፡ ለባሽ
ድንጋይ ፡ ወንዙ ፡ ይናገራል ፡ ነህ ፡ አባት
ታማኝነትህ ፡ ተፈትኖ ፡ የፀና
አትለወጥ ፡ አትደክም ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
አልተገኘም ፡ አይገኝም ፡ አንተን ፡ ሚተካ
ብቻህን ፡ ነህ ፡ ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ከለላ

አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይገባኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይሞላም ፡ በእጄ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይመስለኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
እኔ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እጄ ፡ ባለው
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የታዘዘውን
ቃልህ ፡ ካፍህ ፡ ወጥቶ ፡ መች ፡ ተመልሷል
ሳያደርግ ፡ ሳይፅም ፡ የተላከውን

አንዳንዶቹ ፡ በሰረገላቸው ፡ ሲመኩ
ሌሎች ፡ ደግሞ ፡ ብዛታቸውን ፡ ሲቆጥሩ
ሁሉም ፡ ይኸው ፡ በየተራ ፡ እንዲያው ፡ አለፉ
አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ እንዳማረብህ ፡ ክርህን ፡ አልነኩ
ምክር ፡ ትዕዛዝህ ፡ የፀና ፡ ለዘለአለም
ከአፍህ ፡ ቃል ፡ አንዳች ፡ እንኳን ፡ የሚወድቅ ፡ የለም
ትደምቃለህ ፡ ትከብራለህ ፡ ገና ፡ ገና
መች ፡ ቀመስነው ፡ መች ፡ አየነው ፡ ያንተን ፡ ግርማ

አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይገባኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይሞላም ፡ በእጄ ፡ ያለው
አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ባይመስለኝም ፡ ፊቴ ፡ ያለው
እኔ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እጄ ፡ ባለው