ተነስቷል (Tenestual) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

የትንሳኤው ፡ ጀግና ፡ ነው
የትንሳኤው ፡ ንጉሥ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ተነሳ ፡ መሬቱ ፡ ሳይማስ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ተነስቷል ፡ መቃብር ፡ ሳይማስ

የሞትን ፡ መውጊያ ፡ ሰብሮ ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ
ሕይወቱን ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ለተጎዳው ፡ ካሳ
ይገርመኛል (፪x) ዝም ፡ ብሎ ፡ ይገርመኛል
ይደንቀኛል (፪x) ዝም ፡ ብሎ ፡ ይደንቀኛል

ሰማቹ ፡ ወይ ፡ ቀና ወሬ ሰማችሁ ፡ ወይ ፡ መልካም ፡ ዜና
የሞተው ፡ ተነስቷል ፡ ተብሎ ፡ ሲወራ

ከመሬት ፡ በላይ (፫x) በላይ

አልቻለውም ፡ ሊይዘው
አልቻለውም ፡ ሊያስቀረው
መቃብሩ ፡ ሲከፈት ፡ውጡ ባዶ ፡ ነው

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ ፡ ወደላይ ፡ ያረገው
ይሄ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከሌሎቹ ፡ ልዩ ፡ የሚያደርገው

ኤልሻዳይ ፡ ነው
አዶናይ ፡ ነው
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው

ኤማኦስም ፡ አልወርድም ፡ ቁርጤንም ፡ ሳልሰማ
መቃብር ፡ ውስጥ ፡ ቢሆንም ፡ ድምጽ ፡ አለ ፡ ሚሰማ
ሲስት ፡ ቀን ፡ ሶስት ፡ ለሊት ፡ መሬት ፡ ውስጥ ፡ ቢያድርም
እነሳለሁ ፡ ስላለ ፡ ተሸነፈ ፡ አልልም