ቤቴ በሰላም (Bete Beselam) - ዮሴፍ : አያሌው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ : አያሌው
(Awtaru Kebede)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2006
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 07:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ : አያሌው ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ
ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ

አልቆጥብ አልቀንስ ያረከውን ላዉራ
ታምራትህ በዝቷል የማዳንህ ስራ
የማዳንህ ስራ
አልቆጥብ አልቀንስ አሀሀሀ
ያረከውን ላዉራ አሀሀሀ
ታምራትህ በዝቷል የማዳንህ ስራ
የማዳንህ ስራ

በእንጀራ እና በውሀ ብቻ መች ይኖራል እዚ ምድር ላይ
የኔስ ልብ የሚያርፈው የሚያርፈው የሱን ክብር ሲያይ
በእንጀራ እና በውሀ ብቻ መች ይኖራል እዚ ምድር ላይ
የኔስ ልብ የሚያርፈው የሚያርፈው የሱን ክብር ሲያይ

ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ
ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ

ሠው በሀብቱ ብዛት ለፍቶ ባከማቸዉ ህይወቱ አይለካ
ድጋፍ በሚሆነው በእግዚአብሔር ይሻላል ቢመካ
ሠው በሀብቱ ብዛት ለፍቶ ባከማቸዉ ህይወቱ አይለካ
ድጋፍ በሚሆነው በእግዚአብሔር ይሻላል ቢመካ

የነፍሴን እርሃብ አሀሀሀ
ብር ወርቅ ላይሞላው አሀሀሀ
ሌተቀን ቢለፋ ጎዶሎው ብዙ ነው
ጎዶሎው ብዙ ነው
የነፍሴን እርሃብ አሀሀሀ
ብር ወርቅ ላይሞላው አሀሀሀ
ሌተቀን ቢለፋ ጎዶሎው ብዙ ነው
ጎዶሎው ብዙ ነው

ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ
ቤቴን በሠላም በደግነትህ
ህይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ

ማልጄ በፊቱ አምላኬ እለዋለሁ ባማረ ምስጋና
አይጓደልበት አምልኮ ክብር የሱ ነውና
ማልጄ በፊቱ አምላኬ እለዋለሁ ባማረ ምስጋና
አይጓደልበት አምልኮ ክብር የሱ ነውና

ላንተ ይሁን አምልኮ
ላንተ ይሁን ምስጋና
ላንተ ይሁን አምልኮ
ላንተ ይሁን ምስጋና
ይገባሀልና ጌታዬ ይገባሀልና
ይገባሀልና ወዳጄ ይገባሀልና
ይገባሀልና ጌታዬ ይገባሀልና
ይገባሀልና ወዳጄ ይገባሀልና
ላንተ ይሁን አምልኮ
ላንተ ይሁን ምስጋና
ላንተ ይሁን አምልኮ
ላንተ ይሁን ምስጋና
ይገባሀልና ጌታዬ ይገባሀልና
ይገባሀልና ወዳጄ ይገባሀልና
ይገባሀልና ጌታዬ ይገባሀልና
ይገባሀልና ወዳጄ ይገባሀልና