From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ
ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ
ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን
አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን (፪x)
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል
ሹመት ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ ከዓለም ፡ የተወሰነ
ማንም ፡ የማይቀያይረው ፡ ከላይ ፡ የሆነ
ልጄ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህ ፡ ማዕረጌ ፡ ነው
ውስጤን ፡ መደነቅ ፡ ሞልቶታል ፡ ለእኔ ፡ በሆነው
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል
አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ
ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ
ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን
አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን
በህልሜ ፡ በእውኔ ፡ አስቤ ፡ የማላውቀውን
ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ያልጠበኩትን
ልዘምር ፡ በገናዬን ፡ ላንሳ ፡ ቅኔን ፡ ልደርድር
ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ የሆነውን ፡ ስራህን ፡ ልናገር
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል
አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ
ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ
ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን
አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን
አይቆጠር ፡ እንዲሁ ፡ አይባል ፡ ቸርነትህ
የማይለወጠው ፡ ፍቅርህ ፡ የአባትነትህ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ እገልጸዋለው ፡ ያረክልኝን
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ የበዛው ፡ የዋልክልኝን
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል
እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል
አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ
ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ
ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን
አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን
|