ምህረትህ (Mehereteh) - ዮሴፍ ፡ አያሌው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ አያሌው
(Yoseph Ayalew)

Yoseph Ayalew 2.jpeg


(2)

ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ
(Serayien Yeserahelegn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ አያሌው ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Ayalew)

አንተ ፡ ከወደድከኝ ፡ የሚጠላኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ካጸደከኝ ፡ የሚከሰኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ከወደድከኝ ፡ የሚጠላኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ካጸደከኝ ፡ የሚከሰኝ ፡ ማነው (፪x)
ማነው ፣ ማነው (፫x)

ስሙን ፡ አከብራለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ
ቀንበሬን ፡ ሰባብሮ ፡ እኔን ፡ ፈታ (፪x)
ኀጢአቴም ፡ ተሻረ ፡ ተወገዷል
ምህረቱን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አግኖታል (፪x)
አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
እጅህ ፡ ስለያዘኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
እጅህ ፡ ስለያዘኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)

ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ ጥሎልኛል
እግዚአብሔር ፡ ሞገሴ ፡ ሆኖልኛል (፪x)
ድንቁን ፡ አወራለሁ ፡ በዘመኔ
ድጋፌ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ መድህኔ (፪x)
አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
እጅህ ፡ ስለያዘኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
አባት ፡ ስለሆንከኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
እጅህ ፡ ስለያዘኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)

ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ናት
ዓለምን ፡ በፍቅሩ ፡ የሚመራት (፪x)
ስለወደደንም ፡ አድኖናል
ማንም ፡ አይከሰንም ፡ አጽድቆናል (፪x)

አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለአንተ ፡ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለአንቺ ፡ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለእኛ ፡ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
እጅህ ፡ ስለያዘኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
አባት ፡ ስለሆንከኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ምህረትህ ፡ ገኖልኝ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)

አንተ ፡ ከወደድከኝ ፡ የሚጠላኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ካጸደከኝ ፡ የሚከሰኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ከወደድከኝ ፡ የሚጠላኝ ፡ ማነው (፪x)
አንተ ፡ ካጸደከኝ ፡ የሚከሰኝ ፡ ማነው (፪x)
ማነው ፣ ማነው (፫x)