From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ዮሴፍ ፡ ካሳ (Yosef Kassa)
|
|
፫ (3)
|
ዝምታው (Zemetaw)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ (2018)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ (10)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:59
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች (Albums by Yosef Kassa)
|
|
ሚነጋ ፡ አይመስልም ፡ ሌሊቱ ፡ ረዝሞ
ጨለማውን ፡ አይቶ
ሌሊቱም ፡ ያልፋል ፡ ደግሞም ፡ ይነጋል
ብርሃን ፡ ተክቶ
አይዘኝ ፡ ሃሳብ ፡ ትካዜ
ይሆናል ፡ ሁሉ ፡ በጊዜ (፪x)
አትጠጉት ፡ በቃ ፡ ድንጋይ ፡ አድርጉበት ፡ ሸትቷል ፡ መቃብሩ
ጠብቀነው ፡ ነበር ፡ በጊዜ ፡ እንዲመጣ ፡ አክትሟል ፡ ነገሩ
ሰው ፡ ደክሞት ፡ ሲጨርስ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ይጀምራል
በሞተ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ይፈርዳል ፡ ሕይወት ፡ ይሰጠዋል
ዝምታው ፡ ቢያስገርም ፡ የማያይ ፡ ቢመስልም
አይቸኩል ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ይፈርዳል ፡ በጊዜው
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
ሚነጋ ፡ አይመስልም ፡ ሌሊቱ ፡ ረዝሞ
ጨለማውን ፡ አይቶ
ሌሊቱም ፡ ያልፋል ፡ ደግሞም ፡ ይነጋል
ብርሃን ፡ ተክቶ
አይዘኝ ፡ ሃሳብ ፡ ትካዜ
ይሆናል ፡ ሁሉ ፡ በጊዜ (፪x)
ልቧ ፡ ያዘነባት ፡ ሁሌ ፡ ምታለቅሰው ፡ ልጅ ፡ የሌላት ፡ ሃና
ታሾፍባት ፡ ነበር ፡ ነገ ፡ የሚሆነው ፡ ያልገባት ፡ ፍናና
በጊዜው ፡ ፈረደ ፡ አምላኳ ፡ እንባዋን ፡ አበሰ
ትውልድ ፡ የሚያወሳው ፡ ልጅ ፡ ሰጣት ፡ ሕይወቷ ፡ ተካሰ
ዝምታው ፡ ቢያስገርም ፡ የማያይ ፡ ቢመስልም
አይቸኩል ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ይፈርዳል ፡ በጊዜው
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
አንዳንዶች ፡ እንደዚህ ፡ ናቸው
መከራው ፡ ሲበዛባቸው
እምነታቸውን ፡ ሲጥሉ
አይሰማም ፡ አያይም ፡ ሲሉ
አለ ፡ ሁሉንም ፡ የሚያይ
ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x)
ስለዚህ ፡ አትታበዩ
በኩራት ፡ አትናገሩ
እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል
ይፈርዳል ፡ ይፈርዳል
|