Yosef Kassa/Zemetaw/Yihie New Yegebagn
< Yosef Kassa | Zemetaw
- ውሰድልኝ ዛሬ ከነፍሴ የሆነ አምልኮዬን
- አላገናኘውም ከሁኔታ ጋራ ዝማርዬን
- ተላንት አመስግኜ ዛሬን አላማህም እንዲህ ብዬ
- ይጨምራል እንጂ አላሳንሰውም ምስጋናዬ
- የማየው ነገር ከምስጋናዬ አያግደኝም
- የምሰማው አንተን ከማምለክ አያስቆመኝም
- ምድረበዳዬን አለምልሞታል እያየ አይኔ
- በህሩን ከፍሎ ያሻግረኛል አምናለሁ እኔ
- ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
- ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪)
- የለመንኩትን የጠየኩትን ጥያቄ ሁሉ
- ከምስጋና ጋር እጠብቃለሁ አምኜ ቃሉን
- የከበደኝን ሸክሜን ሁሉ በእርሱ ላይ ጥዬ
- በአንዳች ነገር አልጨነቅም አለ ጌታዬ
- ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
- ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪)
- ደመና የለም አይታየኝም በዓይኔ
- ነፋሥም የለም አይታየኝም በዓይኔ
- ሳላይ አምናለሁ እንዲሀ ይሆናል
- ባዶ ሸልቆ ውኃ ይሞላል
- ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
- ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪)
- ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ
- አይቻለሁኝ ሲሰራ
- ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ
- ክንደ ብርቱ ነው ኃይለኛ
- ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ
- ድንቅ ነው ተአምረኛ
- ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ
- አይቻለሁኝ በዓይኔ
- ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ