የመዳኔ ፡ ነገር (Yemedanie Neger) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 3.jpg


(3)

ዝምታው
(Zemetaw)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር
አሁንም ፡ መልሼ ፡ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር
የመዳኔ ፡ ነገር

ቀሎ ፡ ስለመጣ ፡ አይቀልም ፡ በሕይወቴ ፡ የመስቀሉ ፡ ስራ
በክብር ፡ ታጅቦ ፡ ይመጣል ፡ ሊወስደኝ ፡ አርጐኛል ፡ ሙሽራ
ሰማይ ፡ ደስታ ፡ ሆነ ፡ ዕልልታው ፡ ቀለጠ ፡ በእኔ ፡ መዳን
እንዴት ፡ መታደል ፡ ነው ፡ በበጉ ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መሆን

አጋንንት ፡ ቢወጣ ፡ ሽባ ፡ ቢተረተር
የሞተ ፡ ቢነሳ ፡ ይህም ፡ ያልፋል ፡ ምድር
አይወዳደርም ፡ ይሄኛው ፡ ተአምር
የመዳኔ ፡ ነገር

ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር
አሁንም ፡ መልሼ ፡ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር
የመዳኔ ፡ ነገር

አማኝ ፡ ሞት ፡ አይፈራ ፡ እንግዳ ፡ ነውና ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
ይናፍቃል ፡ እንጂ ፡ ከአምላኩ ፡ ጋር ፡ መኖር ፡ በላይ ፡ በሰማይ
ሰው ፡ ዓለምን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል ፡ መቼ ፡ ይጠቅመዋል
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ለዘላለም ፡ መኖር ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል

ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ሞኝህን ፡ አስፈራራ
ሞት ፡ አይፈራም ፡ አማኝ ፡ ሰማይ ፡ የእርሱ ፡ ስፍራ
ይሄ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ቁሳቁስ ፡ አልቆጥር
የእኔ ፡ ፡ ሃብት ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ የሚሻገር
የመዳኔ ፡ ነገር

ክብር ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ዝና ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ጉልበት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ሃዘን ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ማግኘት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ማጣት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
የማያልፈው ፡ አንድ ፡ ነገር
በሰማያት ፡ ያለ ፡ ክብር
ተጽፎልኝ ፡ ስሜ ፡ በላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ወይ

በዚህ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ደስታ
ሞልቶኛል ፡ ዕልልታ
ለዚህ ፡ ነው ፡ ጩኸቴ
ሰማይ ፡ ቤት ፡ በመግባቴ

ክብር ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ዝና ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ጉልበት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ሃዘን ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ማግኘት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
ማጣት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል
የማያልፈው ፡ አንድ ፡ ነገር
በሰማያት ፡ ያለ ፡ ክብር
ተጽፎልኝ ፡ ስሜ ፡ በላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ወይ