ከኖሩማ (Kenoruma) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 3.jpg


(3)

ዝምታው
(Zemetaw)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ንፋሱ ፡ ነፈሰና ፡ አለፈ
ወጀቡም ፡ ጸጥ ፡ አለ ፡ አለፈ
መንገዴን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው
ይህ ፡ ሁሉ ፡ ለመልካም ፡ የሆነው
ስላለ ፡ ጌታ ፡ አጠገቤ
ስላለ ፡ አባ ፡ አጠገቤ

ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ
ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ
ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች

ስሄድ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ በሕይወት ፡ መንገድ
ምንም ፡ ነገር ፡ አይሆን ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ፈቃድ
አያስጨንቀኝም ፡ ነገ ፡ የሚሆነው
የነፍሴ ፡ ፍጻሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው

የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ የማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ

ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ
ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ
ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች

ሲጸልይ ፡ ዳንኤል ፡ አንተን ፡ ስለጠራ
ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከተቱት ፡ በአንበሳ ፡ እንዲበላ
ይንከባከቡታል ፡ እንኳን ፡ ሊበሉት
ችግር ፡ ይቀየራል ፡ በምቾት

የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ የማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ

ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ከአንተ ፡ የራቀ ፡ የተሰወረብህ
እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሁሉን ፡ የምታውቅ
ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ የሚያስደነግጥህ
እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩን ፡ ሁሉን ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ

መላ ፡ ሕይወቴ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
እድሜ ፡ ዘመኔ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
ነገዬም ፡ ቢሆን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
እስትንፋሴ ፡ እንኳን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ