From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
M
|
ዮሴፍ ፡ ካሳ (Yosef Kassa)
|
|
፫ (3)
|
ዝምታው (Zemetaw)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ (2018)
|
ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
ርዝመት (Len.):
|
6:14
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች (Albums by Yosef Kassa)
|
|
ይውለቅ ፡ ከላዬ ፡ ላይ ፡ ይህ ፡ የክብር ፡ ልብሴ
በፊቱ ፡ ላሸብሽብ ፡ ታመስግነው ፡ ነፍሴ
አይገደኝም ፡ እኔ ፡ ያሉኝን ፡ ቢሉኝ
ታቦቱ ፡ ከፊቴ ፡ ቤቴ ፡ ቀርቦልኝ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ይሁን
ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ይሁን
ደግሞ ፡ ተነሳ ፡ ልቤ ፡ እንደገና
ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ትዝ ፡ አለኝና ፡ ትዝ ፡ አለኝና
አልቻልኩበትም ፡ ዝም ፡ ማለት
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ባርኪው ፡ አምላክሽን ፡
ከወደቅሽበት ፡ ያነሳሽን ፡
ውለታውን ፡ እንዳትረሺ
ለምሥጋን ፡ ሁሌ ፡ ተነሺ
ማን ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
በበረሃው ፡ ላይ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
እየደጋገፈ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
ያም ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
አምልኮዬን ፡ ይዤ ፡ አደባባይ ፡ ልውጣ
ያኮራኛል ፡ እንጂ ፡ አላፍርም ፡ በጌታ
የረዳኝ ፡ ይክበር ፡ ጌታዬ '
ያገዘኝ ፡ ይክበር ፡ ጌታዬ
ደግሞ ፡ ተነሳ ፡ ልቤ ፡ እንደገና
ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ትዝ ፡ አለኝና ፡ ትዝ ፡ አለኝና
አልቻልኩበትም ፡ ዝም ፡ ማለት
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ እያስመለጠ
እባቡን ፡ ጊንጡን ፡ እያስረገጠ
እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ሊዘምር
ተደርጐልኝ ፡ ብዙ ፡ ተዓምር
ማን ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
በበረሃው ፡ ላይ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
እየደጋገፈ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
ያም ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከጐኔ ፡ ሆኖ ፡ ያበረታኝ
አምልኮዬን ፡ ይዤ ፡ አደባባይ ፡ ልውጣ
ያኮራኛል ፡ እንጂ ፡ አላፍርም ፡ በጌታ
የረዳኝ ፡ ይክበር ፡ ጌታዬ '
ያገዘኝ ፡ ይክበር ፡ ጌታዬ
እዩአት ፡ ስትከፋ ፡ ሜልኮል
በአምላኬ ፡ ፊት ፡ ሳሸበሽብ
ውርደት ፡ መስሏት ፡ ክብሬን ፡ መጣሌ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ በሕይወት ፡ መኖሬ
ሰማይን ፡ ለሰራ ፡ ምድርን ፡ ለዘረጋ
ላለና ፡ ለሚኖር ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ እሆናለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሆናለሁ
አባቴ ፡ ነው ፡ እሆናለሁ
እወደዋለሁ ፡ እሆናለሁ
እዩአት ፡ ስትከፋ ፡ ሜልኮል
በአምላኬ ፡ ፊት ፡ ሳሸበሽብ
ውርደት ፡ መስሏት ፡ ክብሬን ፡ መጣሌ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ በሕይወት ፡ መኖሬ
ሰማይን ፡ ለሰራ ፡ ምድርን ፡ ለዘረጋ
ላለና ፡ ለሚኖር ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ እሆናለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሆናለሁ
አባቴ ፡ ነው ፡ እሆናለሁ
እወደዋለሁ ፡ እሆናለሁ
ሕይወቴ ነው ፡ እሆናለው
ኣ...
|