አልለምደውም (Alelemdewem) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 3.jpg


(3)

ዝምታው
(Zemetaw)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ከስሞች ፡ ሁሉ ፡ በላይ
ሁሉን ፡ የሚገዛ ፡ በምድር ፡ ሆነ ፡ በሰማይ

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ

ዓለምደውም ፡ ስጠራው ፡ ኢየሱሴ ፡ ስል
ተስማምቶኛል ፡ ለሕይወቴ
ሥሙ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ

ነፍሴ ፡ አለረካ ፡ አለች ፡ በሌላ ፡ ነገር
አንዴ ፡ ተይዛለች ፡ በስምህ ፡ ፍቅር
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ኢየሱስ ፡ ስልህ
እሰወራለሁኝ ፡ በህልውናህ

ዓለምደውም ፡ ስጠራው ፡ ኢየሱሴ ፡ ስል
ተስማምቶኛል ፡ ለሕይወቴ
ሥሙ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ

ስምህን ፡ ነፍሴ ፡ ትወደዋለች
አንተን ፡ አንተን ፡ በቻ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ትላለች

ዓለምደውም ፡ ስጠራው ፡ ኢየሱሴ ፡ ስል
ተስማምቶኛል ፡ ለሕይወቴ
ሥሙ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ

ድምጽ ፡ ይሰማል ፡ ከሰማያት
ሲዘምሩ ፡ መላእክት
ኢኢየሱስን ፡ ያከብራሉ
ለሥሙ ፡ ይሰግዳሉ