አባት ፡ አለኝ (Abat Alegn) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 3.jpg


(3)

ዝምታው
(Zemetaw)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

አባት ፡ አለኝ ፡ አባት
ሁል ፡ ጊዜ ፡ የምመካበት
ሚረዳኝ ፡ ሚራራልኝ
ከጐኔ ፡ የማይለየኝ
ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ በሕይወቴ
ያሳደገኝ ፡ ከልጅነቴ
እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ
ምሕረቱ ፡ ያቆመኝ

አይተኛም ፡ እርሱ ፡ እኔን ፡ እየጠበቀ
ከክፉ ፡ አውሬ ፡ እየተናጠቀ
ያሳድረኛል ፡ በለምለሙ ፡ ስፍራ
በእጆቹ ፡ ይዞኛል ፡ ክፉን ፡ እንዳልፈራ

ላምልክህ ፡ ወድጄ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
መልካምነትህ ፡ አይተዋል ፡ ዓይኖቼ
ውሰድ ፡ አምልኮዬን ፡ መስዋዕቴን
ዛሬም ፡ አይሰለቸኝ ፡ አንተን ፡ ማመስገን

የወደቀውን ፡ ሰው ፡ አንስቶ
አስውቦ ፡ ታሪኩን ፡ ለውጦ
በምሕረትህ ፡ ቆሞ ፡ እንደገና
ይዞ ፡ መጥቷል ፡ በዙ ፡ ምሥጋና
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡
ባለውለታዬ ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር

አባት ፡ አለኝ ፡ አባት
ሁል ፡ ጊዜ ፡ የምመካበት
ሚረዳኝ ፡ ሚራራልኝ
ከጐኔ ፡ የማይለየኝ
ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ በሕይወቴ
ያሳደገኝ ፡ ከልጅነቴ
እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ
ምሕረቱ ፡ ያቆመኝ

የደከመውን ፡ በፍቅር ፡ ሚያነሳ
ሰው ፡ የረሳውን ፡ ከቶ ፡ የማይረሳ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አይፈርድ
እውነተኛ ፡ አባት ፡ ልጆቹን ፡ ሚወድ

ላምልክህ ፡ ወድጄ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
መልካምነትህ ፡ አይተዋል ፡ ዓይኖቼ
ውሰድ ፡ አምልኮዬን ፡ መስዋዕቴን
ዛሬም ፡ አይሰለቸኝ ፡ አንተን ፡ ማመስገን

የወደቀውን ፡ ሰው ፡ አንስቶ
አስውቦ ፡ ታሪኩን ፡ ለውጦ
በምሕረትህ ፡ ቆሞ ፡ እንደገና
ይዞ ፡ መጥቷል ፡ በዙ ፡ ምሥጋና
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡
ባለውለታዬ ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር