ውለታው ፡ አለብኝ (Weletaw Alebegn) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

አዝ፦ ያደረገልኝን ፡ ውለታውን
ሳስብ ፡ ለእኔ ፡ የሆነውን
አመስግን ፡ ይለኛል ፡ እንደገና
ውስጤ ፡ ይጮህብኝና (፪x)

ከየት ፡ እንደተነሳሁ ፡ የሆነልኝ ፡ ትዝ ፡ አለኝና
በአምላኬ ፡ ፊት ፡ ጨፈርኩኝ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ ክብሬን ፡ ተውኩና
እንዳበደ ፡ ቢያዩኝ ፡ በልባቸው ፡ ቢንቁኝ
ልቤ ፡ አምላኬ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ መች ፡ ትዝ ፡ አሉኝ [1]

ምህረቱን ፡ (እንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
ቸርነቱን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
ጥበቃውን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
አባትነቱን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)

ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ ልሁንለት
ራሤን ፡ ባዋርደው ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሥርዓትስ ፡ ቢሉኝ ፡ መች ፡ ሊገባኝ
ውለታውን ፡ ሳስብ ፡ ይብስብኝ

ያደረገልኝን ፡ ውለታውን
ሳስብ ፡ ለኔ ፡ የሆነውን
አመስግን ፡ ይለኛል ፡ እንደገና
ውስጤ ፡ ይጮህብኝና (፪x)

ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ሲሉኝ ፡ ሮጬ ፡ መጣሁ ፡ ሽቶዬን ፡ ይዤ
ፊቱን ፡ ሳየው ፡ ሰገድኩኝ ፡ እግሩን ፡ ልሳም ፡ ይራስ ፡ በእምባዬ
ምን ፡ ነካው ፡ አትበሉኝ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እስኪ ፡ ተዉኝ
ብዙ ፡ ምህረት ፡ ያገኘሁ ፡ ይቅር ፡ የተባልኩ ፡ ሰው ፡ ነኝ [2]

ምህረቱን ፡ (እንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
ቸርነቱን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
ጥበቃውን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)
አባትነቱን ፡ (አንደ ፡ እኔ ፡ ያየ) ፡ ልቡ ፡ ተነሳ ፡ (ላምልከው ፡ አለ)

ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ ልሁንለት
ራሤን ፡ ባዋርደው ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሥርዓትስ ፡ ቢሉኝ ፡ መች ፡ ሊገባኝ
ውለታውን ፡ ሳስብ ፡ ይብስብኝ

ብቀኝለትም ፡ ብሰግድለትም ፡ ባሸበሽብም ፡ (ለእርሱ)
ህይወት ፡ ለሆነኝ ፡ ሰላም ፡ ለሰጠኝ ፡ ከሞት ፡ ላዳነኝ ፡ (ለእርሱ) (፪x)

ውለታው ፡ (አለብኝ ፡ እኔ) (፰x)

  1. ፪ ሳሙኤል ፮ ፡ ፲፪ - ፲፮ (2 Samuel 6:12-16)
  2. ዮሐንስ ፲፪ ፡ ፩ ፡ ፯ (John 12:1-7)