From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰው ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ ሆይ
ሰው ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ ሆይ
ሰው ፡ ሆይ ፡ (ተው ፡ በለው) (፬x)
ዘሪ ፡ ዘሩን ፡ ሊዘራ ፡ ወጣ ፡ ማልዶ
ክፉ ፡ ነገር ፡ ዘርቶ ፡ የወደደውን ፡ አደርጎ ፡ ሄደ
መልካምና ፡ ክፉ ፡ ዘር ፡ ነበር ፡ በእጁ
ጊዜው ፡ ደረሰና ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ አጨደው ፡ አይ ፡ መከራ
ምን ፡ ይለዋል ፡ መልካሙን ፡ ቢዘራ
ክፉውን ፡ ዘርቶ ፡ መጣበት ፡ መከራ
አዬ ፡ ጉዱ ፡ ባያስተውል ፡ እርሱ
ጊዜው ፡ ደርሶ ፡ መጣበት ፡ መዘዙ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ዘርቶ ፡ ማጨዱ ፡ ግድ ፡ ነበረ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ከዘራው ፡ ቦታ ፡ መብቀል ፡ ጀመረ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ አቤቱ ፡ ማረኝ ፡ ሲል ፡ ተናዘዘ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ሰማይ ፡ ይቅር ፡ ቢል ፡ ምድር ፡ ቂም ፡ ያዘ
ስዘራው ፡ የሚቀለኝ ፡ ሳጭደው ፡ የሚከብደኝ
አለማስተዋሌ ፡ ጉድ ፡ እንዳያረገኝ
እኔም ፡ ፈራሁኝ ፡ አይ ፡ ጉዴ (፪x)
ክፉ ፡ ዘርቶ ፡ ማጨዱ ፡ ከበደው
ሀዘኑም ፡ በረታ ፡ አሳመመው
ሲዘራ ፡ መች ፡ እንደዚህ ፡ መሰለው
መከራ ፡ አስተማረው
(አስተዋይ ፡ ተማረ ፥ አስተዋይ)
አሁን ፡ እኔም ፡ ለራሴ ፡ ፈራሁኝ
የምዘራው ፡ መልሶ ፡ እንዳያንቀኝ
የማደርገውን ፡ ሁሉ ፡ እንዳስተውል ፡ አስተዋይ ፡ አርገኝ
(አስተዋይ ፡ ተማረ ፥ አስተዋይ)
ክፉ ፡ ዘርን ፡ ሳያስተውል ፡ ጥሎ
ተቀመጠ ፡ አገር ፡ ሰላም ፡ ብሎ
ሲቃይ ፡ ያዘው ፡ ቀን ፡ ጠበቀውና
ዘርቶ ፡ ማጨድ ፡ ተወስኗልና
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ዘርቶ ፡ ማጨዱ ፡ ግድ ፡ ነበረ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ከዘራው ፡ ቦታ ፡ መብቀል ፡ ጀመረ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ አቤቱ ፡ ማረኝ ፡ ሲል ፡ ተናዘዘ
(የዘራውን ፡ አገኘ) ፡ ሰማይ ፡ ይቅር ፡ ቢል ፡ ምድር ፡ ቂም ፡ ያዘ
ስዘራው ፡ የሚቀለኝ ፡ ሳጭደው ፡ የሚከብደኝ
አለማስተዋሌ ፡ ጉድ ፡ እንዳያረገኝ
እኔም ፡ ፈራሁኝ ፡ አይ ፡ ጉዴ (፪x)
“በስውር ፡ የሚሰራ ፡ በግልጽ ፡ እንዲከፈለው
ዘርቶ ፡ እንደሚታጨድ ፡ ማነው ፡ የሚያስተውለው
የምን ፡ ጉድ ፡ መጣብኝ ፡ ብለህ ፡ እንዳትፈራ
የትላንት ፡ ስህተትህ ፡ መከራን ፡ ሲያፈራ
ጌታማ ፡ ምሮኛል ፡ ስጋ ፡ መች ፡ ሊለቀኝ
የዘራሁትን ፡ ሁሉ ፡ ማጨድ ፡ አይቀርልኝ
ሥጋ ፡ በሥጋ ፡ ሳይቀጣ ፡ አይቀርም ፡ እንደሚል ፡ በቃሉ
ዛሬ ፡ ሚዘራው ፡ ነገ ፡ ይበቅላልና ፡ ምከሩ ፡ ተው ፡ በሉ
በል ፡ እንግዲህ ፡ አይዞህ ፡ አሁንም ፡ ጊዜ ፡ አለህ
የኋላህን ፡ ትተህ ፡ የፊትህን ፡ እያየህ
መልካም ፡ መልካሙን ፡ ብቻ ፡ ዝራ
ሕይወት ፡ እንዳይሆንብህ ፡ መከራ”
ክፉ ፡ ዘርቶ ፡ ማጨዱ ፡ ከበደው
ሀዘኑም ፡ በረታ ፡ አሳመመው
ሲዘራ ፡ መች ፡ እንደዚህ ፡ መሰለው
መከራ ፡ አስተማረው
(አስተዋይ ፡ ተማረ ፥ አስተዋይ)
አሁን ፡ እኔም ፡ ለራሴ ፡ ፈራሁኝ
የምዘራው ፡ መልሶ ፡ እንዳያንቀኝ
የማደርገውን ፡ ሁሉ ፡ እንዳስተውል ፡ አስተዋይ ፡ አርገኝ
(አስተዋይ ፡ ተማረ ፥ አስተዋይ)
ሰው ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ ሆይ
ሰው ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ ሆይ
ሰው ፡ ሆይ ፡ (ተው ፡ በለው) (፬x)
|