መኖር ፡ አልችልም (Menor Alchelem) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ሁልጊዜ ፡ ምናፍቅህ
የነፍሴ ፡ ጥማት ፡ የምትወድህ
ልዑል ፡ ነህ ፡ ለእኔ
እርሱ ፡ ነው ፡ ረሃቤ

ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም
ታውቃለህ ፡ አቅም ፡ እኔ ፡ የለኝም
ኢየሱሴ ፡ የእኔ
አትሂድብኝ ፡ ከእኔ

አዝ፦ አትሂድብኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝም (፪x)

ባጠፋም ፡ ልጅህ ፡ ነኝ ፡ ቅጣኝ
ግን ፡ መንፈስህ ፡ እንዳይርቀኝ
የሕይወት ፡ እስትንፋሴ
ህልውናህ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ

ስትርቀኝ ፡ ይከፋኛል
አንተን ፡ መፍራት ፡ ይከብደኛል
የምትረዳኝ ፡ ረድኤቴ
አትሂድ ፡ ከሕይወቴ

አዝ፦ አትሂድብኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝም

ዝናህ ፡ ሀብት ፡ ሞልቶ ፡ ጐተራዬም ፡ ቢሞላም ፡ አዬ
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ (፪x)

መኖር ፡ ይከብደኛል ፡ ሕይወትም ፡ ይታክተኛል
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጎኔ (፪x)

አባብዬ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ ጠዋትም ፡ ማታ
ህልውናህ ፡ መገኘት ፡ ደስታን ፡ አጠገበኝ ፡ ፊትህ (፪x)

ፊትህን ፡ ሳየው ፡ ውስጤን ፡ ደስታ ፡ ትሞላኛለህ
ምንም ፡ ባይኖረኝ ፡ ምንም ፡ አንተው ፡ ትበቃኛለህ (፪x)

መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ (፭x)