መድኃኒያለም (Medehanialem) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

“ስብሐተ-እግዚአብሔር ፡ ይነግር ፡ አፉየ ፡ ኩሉ ፡ ዘስጋ ፡ ይባርክ
ለሥሙ ፡ ቅዱስ ፡ ለዓለም ፡ ወለዓለመ-ዓለም”

አሜን ፡ ሀሌሉያ ፡ እያሉ
ቅዱስ ፡ አለ ፡ እርሱ ፡ ዘምሩ
ዛሬም ፡ እርሱን ፡ የምትፈሩ
አምላካችሁን ፡ አመስግኑ (፪x)

ከድንግል ፡ ማርያም ፡ ከብፅህት ፡ ተወልዶ
ወደ ፡ ምድር ፡ መጣ ፡ ዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ወዶ
በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ሁሉን ፡ ሊያስታርቅ
የባርያን ፡ መልክ ፡ ይዞ ፡ ወረደ ፡ ያለም ፡ መድሐኒት

የድሃደግ ፡ አባት ፡ የመበለት ፡ ዳኛ
እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ ሞተልን ፡ ስለኛ
የሞትን ፡ ጣር ፡ ሁሉ ፡ አጥፍቶ ፡ ተነሳ
የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ ፈረሰ ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ

ተስፋ ፡ የለኝ ፡ ብሎ ፡ ውስጡ ፡ ባዘነዉ
ሰው ፡ ለማይረዳው ፡ ልቡን ፡ ሚያልበዉ
እንባውን ፡ አብሰህ ፡ አቅፈህ ፡ ምታጽናና
ክብርና ፡ ሞገስ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና

በአብ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ (መድኃኒያለም)
ስለ ፡ እኛ ፡ የሞተው ፡ (መድኃኒያለም)
ከሞት ፡ የተነሳው ፡ (መድኃኒያለም)
በክብር ፡ ያረገው ፡ አዬ ፡ (መድኃኒያለም)
በዙፋኑ ፡ ያለው ፡ (መድኃኒያለም)
ደግሞም ፡ የሚመጣው ፡ አዬ ፡ (መድኃኒያለም)

እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ
ቸርነቱን ፡ ተናገሩ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም)
ሰማያትን ፡ ሰራ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም)
ምድርን ፡ ዘረጋ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም)
መላዕክት ፡ ሰገዱ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም)
ይገባዋል ፡ አሉ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም)

ኧኸ ፡ ኧኸ

ይገባዋል ፡ ይገባዋል
ይገባዋል ፡ ይገባዋል ፡ (ታርዷልና) (፫x)

በከበሮ ፡ (አመስግኑት)
በመሰንቆ ፡ (አመስግኑት)
በበገና ፡ (አመስግኑት)
በዕልልታ ፡ (አመስግኑት) (፪x)

ኧኸ ፡ ኧኸ

ይገባዋል ፡ ይገባዋል
ይገባዋል ፡ ይገባዋል ፡ (ታርዷልና) (፫x)