ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉ (Gizie Alew Lehulu) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ቃልህን ፡ ሰምቼ ፡ ተጽናናሁኝና
ይፈጸማል ፡ ብዬ ፡ ነገን ፡ ጠበቅኩና
ጊዜው ፡ ሲገፋ ፡ አስጨነቀኝ
ያልከኝም ፡ ምንም ፡ አልሆነልኝ
ይልቁን ፡ መከራ ፡ ሆነብኝ
ምንድነው ፡ ጉዱ ፡ መላ ፡ በሉኝ

ወተትና ፡ ማርን ፡ የምታፈስ ፡ ሀገር
አወርሳችኋለሁ ፡ ብለህ ፡ ለእስራኤል [1]
መንገድ ፡ ሲጀምሩ ፡ መከራቸው በዛ
የተናገርካቸው ፡ ሁሉ ፡ እስኪረሳ [2]

ያልከው ፡ ግን ፡ ሌላ
የሚሆነው ፡ ሌላ (፪x)

መች ፡ በረሃ ፡ ቀሩ ፡ ቃሉ ፡ ተፈፀመ
አትዘገይም ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ሁሉ ፡ ሆነ [3]
ምንም ፡ ብትዘገይም ፡ ትመጣለህና
እጠብቅሃለሁ ፡ የእኔም ፡ ቀን ፡ አለና

ያልከው ፡ ግን ፡ ሌላ
የሚሆነው ፡ ሌላ (፪x)

አንተ ፡ ያልከኝ ፡ ሌላ ፡ ነው
የሚሆንብኝ ፡ ሌላ ፡ ነው
ምንድነው ፡ ነገሩ ፡ ወዴት ፡ ነው
ሚስጥሩ ፡ አስተምረኝ

አዝ፦ (ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ኧረ ፡ ነፍሴ ፡ ረጋ ፡ በዪልኝ
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ያደርገዋል ፡ እርሱ ፡ ካለኝ
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ሳይፈፀም ፡ ጊዜው ፡ ቢገፋም
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ እጠብቃለሁ ፡ የትም ፡ አልሄድም (፪x)

ዮሴፍ ፡ ወንድሞቹ ፡ ሲሰግዱለት፡ አየ
እንደምታከብረው ፡ እንዲነግስ ፡ አለመ [4]
ነገር ፡ ግን ፡ ሲነሳ ፡ ሊገድሉት ፡ ተነሱ
በግዞት ፡ ተጣለ ፡ ህልሞቹም ፡ ተረሱ [5]

ያልከው ፡ ግን ፡ ሌላ
የሚሆነው ፡ ሌላ (፪x)

ዘመናት ፡ ቢፈጅም ፡ ህልሙ ፡ ተፈጸመ
የማይሆን ፡ ቢመስልም ፡ እንዳየው ፡ ግን ፡ ሆነ
በለሱን ፡ የሚጠብቅ ፡ ፍሬዋን ፡ ሊበላ
ለታገሱ ፡ ሁሉ ፡ ጊዜ ፡ አለህና

ያልከው ፡ ግን ፡ ሌላ
የሚሆነው ፡ ሌላ (፪x)

አንተ ፡ ያልከኝ ፡ ሌላ ፡ ነው
የሚሆንብኝ ፡ ሌላ ፡ ነው
ምንድነው ፡ ነገሩ ፡ ወዴት ፡ ነው
ሚስጥሩ ፡ አስተምረኝ

አዝ፦ (ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ኧረ ፡ ነፍሴ ፡ ረጋ ፡ በይልኝ
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ያደርገዋል ፡ እርሱ ፡ ካለኝ
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ ሳይፈፀም ፡ ጊዜው ፡ ቢገፋም
(ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም) ፡ እጠብቃለሁ ፡ የትም ፡ አልሄድም (፪x)

አምላኬ ፡ ጊዜው ፡ ሲሄድብኝ ፡ መላ ፡ ፍለጋ
አጋር ፡ ቤት ፡ ገብቼ ፡ እንዳልጐዳ
አስተዋይ ፡ አርገኝ ፡ ትዕግስትን ፡ ስጠኝ (፪x)

ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ፡ አላፍርምና
በራስህ ፡ ጊዜ ፡ ይሆናልና
እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ ታጋሽ ፡ አርገኝ (፪x)

  1. ዘፍጥረት ፫ ፡ ፯ - ፲ (Genesis 3:7-10)
  2. ዘጸዓት ፲፭ ፡ ፳፪ - ፲፯ ፡ ፲፭ (Exodus 15:22-17:15); ዘጸዓት ፴፪ ፡ ፩ - ፴፫ ፡ ፮ (Exodus 32:1-33:6); ዘኁልቁ ፲፩ ፡ ፩ - ፲፪ ፡ ፲፮ (Numbers 11:1-12:16) ዘኁልቁ ፳፭ ፡ ፩ - ፮ (Numbers 25:1-6)
  3. ኢያሱ ፮ ፡ ፩ - ፳፯ (Joshua 6:1-27)
  4. ዘፍጥረት ፴፯ ፡ ፭ - ፲ (Genesis 37:5-10)
  5. ዘፍጥረት ፴፯ ፡ ፲፰ - ፴፮ (Genesis 37:18-36)