ጌታ ፡ ከኛ ፡ ጋር (Gieta Kegna Gar) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ሊወጋኝ ፡ ጠላት ፡ ከቦኝ ፥ ሲፎክር ፡ ሲያስፈራራኝ
አምላኬን ፡ ስመለከት ፥ ልቤ ፡ ተሞላ ፡ በእምነት
የልብ ፡ ዓይኖቼን ፡ ሲያበራ ፥ አየሁ ፡ የእሳት ፡ ሰረገላ
በል ፡ ግጠማቸው ፡ ውጣና ፥ አስቀድምልኝ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ጌታ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር) ፡ በመንፈሱ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር)
ኢየሱስ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር) ፡ በመንፈሱ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር)

ሰልፉ ፡ ሲበዛ ፡ ፈራሁኝ ፡ ብዬ
አምላኬን ፡ ጠየቅኩ ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ብዬ
ልጄ ፡ ምሥጋና ፡ ጀምር ፡ አለኝ
በድብቅ ፡ ጦሩ ፡ ሊፈጅልኝ

ጠላት ፡ ወደቀ ፡ (ምሥጋናን ፡ ይዤ)
ተንኮታኮተ ፡ (ምሥጋናን ፡ ይዤ)
ቃሉን ፡ ለብሼ ፡ (ምሥጋናን ፡ ይዤ)
ሰይፌን ፡ ይዤ (ምሥጋናን ፡ ይዤ)

አትደናገጥ ፡ በምትሰማው ፡ በሟርት ፡ በዛቻቸው
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ይበልጣልና ፡ ታድያ ፡ ሳቅባቸው
ቀድሞም ፡ ጠላትህ ፡ ወድቋልና ፡ በእምነት ፡ ጀምር ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ጌታ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር) ፡ በመንፈሱ ፡ (ከእኛ፡ ጋር)
ኢየሱስ ፡ (ከእኛ ፡ ጋር) ፡ በመንፈሱ ፡ (ከእኛ፡ ጋር)

ጠላቱ ፡ የተቀጣ ፡ (ጠላቱ ፡ የተቀጣ)
ለአምላኩ ፡ ክብር ፡ ያምጣ ፡ (ለአምላኩ ፡ ክብር ፡ ያምጣ)
ይደርደር ፡ በገናው ፡ (ይደርደር ፡ በገናው)
ይመታ ፡ ከበሮው ፡ (ይመታ ፡ ከበሮው )

ምሥጋና ፡ (ለእርሱ) ፡ እልልታ ፡ (ለእርሱ)
ምሥጋና ፡ (ለእርሱ) ፡ እልልታ ፡ (ለእርሱ)
ምሥጋና ፡ (ለእርሱ) ፡ እልልታ ፡ (ለእርሱ) (፪x)

(ወላይትኛ)