From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በባርነት ፡ በቀምበር ፡ ተይዞ
የተስፋው ፡ ሕዝብ ፡ በሃዘን ፡ ተውጦ
የሰቆቃ ፡ ጩኸቱን ፡ ሰማና
አሳረው ፡ ታደገውና
አቤት ፡ የእርሱ ፡ ሥራ
ነፃነቴን ፡ ቃሉ ፡ ነገረኝ
እኔን ፡ እመን ፡ ቀና ፡ በል ፡ አለኝ
ተፈትተሃል ፡ ምንድነው ፡ ጭንቀት
መጠራትህ ፡ ለነፃነት
አቤት ፡ የእርሱ ፡ ሥራ
ከላይ ፡ ወረደ ፡ ሕዝቡን ፡ ሊያሳርፍ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ
(ከላይ ፡ ወረደ ፡ ሕዝቡን ፡ ሊያሳርፍ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ)
የታሰሩትን ፡ ነፃ ፡ ሊያወጣ ፡ መፈታትን ፡ ይዞ
(የታሰሩትን ፡ ነፃ ፡ ሊያወጣ ፡ መፈታትን ፡ ይዞ)
ቀንበር ፡ ተሰብሯል ፡ አይዞህ ፡ አትፍራ ፡ ተረጋግተህ ፡ ኑር
(ቀንበር፡ ተሰብሯል ፡ አይዞህ ፡ አትፍራ ፡ ተረጋግተህ ፡ ኑር)
ተከፍቷል ፡ በሩ ፡ አምነህ ፡ ተራመድ ፡ አለኝ ፡ እግዚአብሔር
(ተከፍቷል፡ በሩ ፡ አምነህ ፡ ተራመድ ፡ አለኝ ፡ እግዚአብሔር)
(ፈቶኛልና) ፡ የኋላዬን ፡ አላይ
(ፈቶኛልና) ፡ የፊት ፡ የፊቴን ፡ እንጂ
(ፈቶኛልና) ፡ አዕምሮዬ ፡ ታድሷል
(ፈቶኛልና) ፡ ነፃነቴን፡ ላውጅ
(ፈቶኛልና) ፡ በፊቱ ፡ እዘላለሁ
(ፈቶኛልና) ፡ እንደተፈታ ፡ ሰው
(ፈቶኛልና) ፡ ጠላቴም ፡ ይፈር ፡ ይፈር
(ፈቶኛልና) ፡ የፈታኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
(ነፃ ፡ ላወጣን ፡ ለጌታ) ፡ ምሥጋና
(ነፃ ፡ ላወጣን ፡ ለጌታ) ፡ እልልታ
(ነፃ ፡ ላወጣን ፡ ለጌታ) ፡ ዘምሩ
(ነፃ ፡ ላወጣን ፡ ለጌታ) ፡ እልል ፡ በሉ
. (1) .
(ነፃ) ፡ ከሀጥያት ፡ (ነፃ) ፡ ከእስራት
(ነፃ) ፡ ከፍርሃት ፡ (ነፃ) ፡ ነፃ ፡ ነኝ (፪x)
ይኸው ፡ እልልታ (፰x)
የፈታኝ ፡ ነገረኝ ፡ ቀሰቀሰኝና
ቀንበርህ ፡ ተሰብሯል ፡ በል ፡ ሂድ ፡ ተነሳና
ተፈቶ ፡ ዝም ፡ የለም ፡ ይሰማል ፡ ምሥጋና
የዘመናት ፡ ታሪክ ፡ ተለውጧልና
ለፈታኝ ፡ (እኔ ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና)
ላዳነኝ ፡ (እኔ ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና)
ለጌታ ፡ (እኔ ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና)
ለኢየሱሴ ፡ (እኔ ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና) (፪x)
ይኸው ፡ እልልታ (፰x)
|