From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አምላክ ፡ ሰውን ፡ ሰራ ፡ መልኩን ፡ ፈለገና
አብሮት ፡ እንዲኖር ፡ ፍቅር ፡ ያዘውና
የሰው ፡ ልጅ ፡ አመፀ ፡ ልቡን ፡ አደንድኖ
አውቆ ፡ እንዳልሰማ ፡ ጆሮ ፡ ዳባ ፡ ብሎ
የአምላክ ፡ ዓላማ ፡ ሰውን ፡ ሲፈጥር
ምድርን ፡ ገዝቶ ፡ እንዲኖር
አትንካ ፡ ያለውን ፡ ፍሬን ፡ ሲበሉ
ባለመታዘዝ ፡ ከእርሱ ፡ ተጣሉ
ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
ፍቅር ፡ ግድ ፡ አለው ፡ ሞቶ ፡ ሊያድናት
መጥቶ ፡ ሊወስዳት ፡ አጭቷት ፡ ሄደ
እንድትዘጋጅ ፡ ጊዜ ፡ ቢሰጣት
ውበቷ ፡ ጠፋ ፡ ይባስ ፡ ተካደ
ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ ፡ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ ፡ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
የሃይማኖት ፡ ቤት ፡ አንቺን ፡ ለሚያይ
ወገኛ ፡ ግብዝ ፡ ፈሪሳዊ
በአንደበትሽ ፡ ታከብሪዋለሽ
ልብሽ ፡ እርቆ ፡ አንቺ ፡ አስመሳይ
ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
አንድ ፡ አካል ፡ አርጐ ፡ ሰርቶሽ ፡ ነበረ
ጐራ ፡ ለይተሽ ፡ ፈራርሰሽ
የቀድሞ ፡ መልክሽ ፡ ውበትሽ ፡ የለም
ተይ ፡ ተመለሺ ፡ ሳይለይሽ
ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ ፡ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ
ኢየሩሳሌም ፡ ሆይ ፡ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
አምላክ ፡ አለቀሰ ፡ ተረሳሁኝ ፡ ብሎ
ጅራፉን ፡ አነሳ ፡ ቤቱ ፡ ተመሳቅሎ
መች ፡ እንዲህ ፡ አበጀሽ ፡ ተለውጧል ፡ መልክሽ
ቀናተኛ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሌላ ፡ ያሰኘሽ ፡ ለታ
እወድሽ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ሙሽራዬ ፡ ሆይ
ተውበሽ ፡ ጠብቂኝ ፡ መጽዳትሽን ፡ ልይ
መጥቼ ፡ እንደወስድሽ ፡ ወደኔ ፡ ተመለሺ
እኔ ፡ ቅዱስ ፡ ነኝና ፡ ተነሽ ፡ ደሜን ፡ እዪና
የት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ (ሙሽራይቱ)
ናፍቆሻል ፡ እርሱ ፡ (ሙሽራይቱ)
በይ ፡ ተዘጋጂ ፡ (ሙሽራይቱ)
ደርሷል ፡ ሰዓቱ ፡ (ሙሽራይቱ)
ነቅተሽ ፡ ጠብቂው ፡ (ሙሽራይቱ)
በንጹህ ፡ ሕይወት ፡ (ሙሽራይቱ)
የአንቺ ፡ ትጉነት ፡ (ሙሽራይቱ)
የእርሱ ፡ ፍጥነት ፡ (ሙሽራይቱ)
ምፅአቱ ፡ ቀርቧልና (፬x)
|