From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አገኘሁኝ ፡ ብዬ ፡ አልፈነድቅም
አጣሁኝም ፡ ብዬ ፡ አምልኮ ፡ አልተውም
መዳኔ ፡ ይበቃኛል ፡ ለምሥጋና
የእግዚአብሔር ፡ ልጅነት ፡ አለኝና (፪x)
የደህንነቴ ፡ ነገር ፡ ከሞት ፡ መዳኔ
ጌታዬን ፡ ለማመስገን ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ለእኔ
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ እፈር ፡ እላማርር
ብሞትም ፡ ያድነኛል ፡ እግዚእብሔር
(አልተውም) ፡ ጌታዬን ፡ ማመስገን
(አልተውም) ፡ ወጀቡ ፡ ቢበዛ
(አልተውም) ፡ እንደውም ፡ ልጨምር
(አልተውም) ፡ ምሥጋናዬን ፡ ላብዛ (፪x)
ለእኔ ፡ (ሁልጊዜ ፡ ማመስገኔ ፡ ምክንያቴ ፡ ነው ፡ መዳኔ)
ሁሌ ፡ (ሁልጊዜ ፡ ማመስገኔ ፡ ምክንያቴ ፡ ነው ፡ መዳኔ) (፪x)
አገኘሁኝ ፡ ብዬ ፡ አልፈነድቅም
አጣሁኝም ፡ ብዬ ፡ አምልኮ ፡ አልተውም
መዳኔ ፡ ይበቃኛል ፡ ለምሥጋና
የእግዚአብሔር ፡ ልጅነት ፡ አለኝና (፪x)
ዛሬ ፡ በበረከቱ ፡ ቢባርከኝ
የሰጠኝን ፡ መልሶ ፡ ቢወስድብኝ
እግዚአብሔር ፡ ሰጠ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነሳ
ሥሙ ፡ ይባረክልኝ ፡ አምልኮ ፡ ላብዛ
(አልተውም) ፡ ጌታዬን ፡ ማመስገን
(አልተውም) ፡ ወጀቡ ፡ ቢበዛ
(አልተውም) ፡ እንደውም ፡ ልጨምር
(አልተውም) ፡ ምሥጋናዬን ፡ ላብዛ (፪x)
ለእኔ ፡ (ሁልጊዜ ፡ ማመስገኔ ፡ ምክንያቴ ፡ ነው ፡ መዳኔ)
ሁሌ ፡ (ሁልጊዜ ፡ ማመስገኔ ፡ ምክንያቴ ፡ ነው ፡ መዳኔ) (፪x)
በላይ ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለ ፡ የሚሉ
ደስ ፡ ይበላቸው ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
ደስታዬ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
እረፍቴ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
ሰላሜ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
መዳኔ ፡ (ነው ፡ መዳኔ) (፪x)
በላይ ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለ ፡ የሚሉ
ደስ ፡ ይበላቸው ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
ደስታዬ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
እረፍቴ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
ሰላሜ ፡ (ነው ፡ መዳኔ)
መዳኔ ፡ (ነው ፡ መዳኔ) (፪x)
ሰላሜ ፡ (ነው ፡ መዳኔ) ፡ መዳኔ ፡ (ነው ፡ መዳኔ) (፪x)
|