አለብኝ ፡ ትዝታ (Alebegn Tezeta) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

አዝ፦ እኔ ፡ የማይረሳኝ ፡ ውለታ
አለብኝ ፡ አንድ ፡ ትዝታ
ቀራንዮ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ
ሞቶ ፡ ያዳነኝ (፪x)

እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበህ ፡ የሞትክልኝ
ተሰቃየህልኝ ፡ መርገሜን ፡ ወሰድከው ፡ ልታድነኝ
ልጅህ ፡ ነኝ ፡ በጣር ፡ የወለድከኝ ፡ ሕይወትና ፡ ሰላም ፡ የሆንከኝ
በሞትህ ፡ እኔን ፡ ስታድነኝ ፡ አየሁ ፡ የመስቀሉ ፡ ፍቅርህን

(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ለኔ ፡ የዋልክልኝ ፡ አለብኝ ፡ ውለታ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ተሰቃየህልኝ ፡ ሞትክልኝ ፡ ጎልጎታ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ አንተን ፡ ባመልክህ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ምክንያቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የመስቀል ፡ ፍቅርህ

አዝ፦ እኔ ፡ የማይረሳኝ ፡ ውለታ
አለብኝ ፡ አንድ ፡ ትዝታ
ቀራንዮ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ
ሞቶ ፡ ያዳነኝ (፪x)

አምላክ ፡ ሆነህ ፡ ሳለህ ፡ ሲያንገላቱህና ፡ ሲያፌዙብህ
እንደወንጀለኛ ፡ አስረው ፡ ሲገርፉህስ ፡ መች ፡ ራሩልህ
ሲንቁህ ፡ ሲሳበቁብህ ፥ መልስም ፡ አልነበረህ ፡ ሲወግሩህ
ለኔ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ የሆነው ፥ እንዴት ፡ እንድትወደኝ ፡ እንዳየው

(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ለኔ ፡ የዋልክልኝ ፡ አለብኝ ፡ ውለታ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ተሰቃየህልኝ ፡ ሞትክልኝ ፡ ጎልጎታ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ አንተን ፡ ባመልክህ
(አልረሳውም ፡ እኔ) ፡ ምክንያቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የመስቀል ፍቅርህ

ለኔ ፡ ነው ፡ ለኔ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለኔ (፭x)