የእኔ ፡ ነህ (Yenie Neh) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 1.jpg


(1)

ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው
(Nuroyie Bekidan New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

 
አዝ፦ የእኔ ፡ ነህ (፫x) ፡ የማለውጥህ
ጌታዬ ፡ የእኔ ፡ ነህ
የአንተው ፡ ነኝ (፫x) ፡ የማትተወኝ
እኔስ ፡ የአንተው ፡ ነኝ

ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የምወድህ
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ላልፈልግህ
ሕይወቴን ፡ ለወጥከው ፡ ወድሃለው ፡ አልከኝ
ሰላምን ፡ ሰጥተኽኝ ፡ ልጅህ ፡ አደረከኝ
(፪x)

ማግኘት ፡ ማጣቴ ፡ መውጣት ፡ መውረዴ
አይለየኝም ፡ ከአንተ ፡ ፍቅር
እንዴት ፡ ይኬዳል ፡ ወዴት ፡ ይኬዳል
ከአንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ እያለ
አልመኘውም ፡ አልፈልገውም ፡ አንተ ፡ የሌለህበትን
ዘመኔ ፡ ይለቀ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ የእውነት ፡ እየወደድኩህ

እኔማ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለው
እኔማ ፡ ማሄጃም ፡ የለኝም
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ
እኔማ ፡ ሕይወትምሰላም ፡ የለኝም (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ነህ (የእኔ ፡ ነህ) (፫x) ፡ የማለውጥህ
ጌታዬ ፡ የእኔ ፡ ነህ
(የአንተው ፡ ነኝ) የአንተው ፡ ነኝ (፫x) ፡ የማትተወኝ
(እኔስ ፡ የአንተው ፡ ነኝ)

አልፈልግም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
ምን ፡ ሊጠቅመኝ ፡ ምን ፡ ሊረባ
ተመችተኽኛል ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ፍቅር
አንተው ፡ ትበቃለህ ፡ ብቻህን ፡ እግዚአብሔር
(፪x)

ማግኘት ፡ ማጣቴ ፡ መውጣት ፡ መውረዴ
አይለየኝም ፡ ከአንተ ፡ ፍቅር
እንዴት ፡ ይኬዳል ፡ ወዴት ፡ ይኬዳል
ከአንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ እያለ
አልመኘውም ፡ አልፈልገውም ፡ አንተ ፡ የሌለህበትን
ዘመኔ ፡ ይለቀ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ የእውነት ፡ የወደድኩህ

(እኔማ) እኔማ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለው
እኔማ ፡ ማሄጃም ፡ የለኝም
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ
እኔማ ፡ ሕይወትምሰላም ፡ የለኝም (፪x)