ስለ ፡ ምህረቱ (Sele Meheretu) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 1.jpg


(1)

ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው
(Nuroyie Bekidan New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

 
አዝ፦ ስለ ፡ ምህረቱ ፡ ስለ ፡ እርሱ ፡ ዝና
ሰምቼ ፡ መጣሁ ፡ ሁሉን ፡ ተውኩና
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ አዩት ፡ ዐይኖቼ
እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረሁ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቼ (፪x)
እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረሁ ፡ ሰላም ፡ አግኝቼ

ነፍሴ ፡ የወደደችው ፡ እርሱን
አይሆንላትም ፡ ሌላ ፡ ነገረ
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይዟታል ፡ ፍቅር
የለም ፡ አለች ፡ ከቶ ፡ እንደእግዚአብሔር
ቸርነቱ ፡ ምህረቱ ፡ የበዛ
አይገኝም ፡ የለም ፡ እንደጌታ

አየሁ ፡ ምህረቱን ፤ አየሁ ፡ ቸርነቱን
አየሁ ፡ ለተጠጋው ፤ አየሁ ፡ ሰው ፡ መውደዱን
አየሁ ፡ ሁልጊዜ ፤ አየሁ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
አየሁ ፡ እንደማይተወኝ ፤ አየሁ ፡ እሱን ፡ ስፈራ

ለጌታ ፡ ለቸርነቱ ፤ ለጌታ ፡ ምሥጋናን ፡ አምጡ
ለጌታ ፡ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ፡ ለጌትነቱ
ለጌታ ፡ ይዘመርለት ፤ ለጌታ ፡ ይሁን ፡ ምትሉ
ለጌታ ፡ ለቸሩ ፡ ጌታ ፤ ለጌታ ፡ እስኪ ፡ እልል ፡ በሉ
ለጌታ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፤ ለጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ቢሰዋ
ለጌታ ፡ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ፡ አዳኝ ፡ ነውና

አዝ፦ ስለ ፡ ምህረቱ ፡ ስለ ፡ እርሱ ፡ ዝና
ሰምቼ ፡ መጣሁ ፡ ሁሉን ፡ ተውኩና
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ አዩት ፡ ዐይኖቼ
እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረሁ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቼ (፪x)
እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረሁ ፡ ሰላም ፡ አግኝቼ

ያ ፡ ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ሲያቅድ
በየቀኑ ፡ ወጥመዱን ፡ ሲያጠምድ
ቢሆንለት ፡ ሕይወቴን ፡ ሊያጠፋ
ሳያቋርጥ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ለፋ
ኢየሱሴ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነበረ
የጠላቴም ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ

አየሁ ፡ ምህረቱን ፤ አየሁ ፡ ቸርነቱን
አየሁ ፡ ለተጠጋው ፤ አየሁ ፡ ሰው ፡ መውደዱን
አየሁ ፡ ሁልጊዜ ፤ አየሁ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
አየሁ ፡ እንደማይተወኝ ፤ አየሁ ፡ እሱን ፡ ስፈራ

ለጌታ ፡ ለቸርነቱ ፤ ለጌታ ፡ ምሥጋናን ፡ አምጡ
ለጌታ ፡ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ፡ ለጌትነቱ
ለጌታ ፡ ይዘመርለት ፤ ለጌታ ፡ ይሁን ፡ ምትሉ
ለጌታ ፡ ለቸሩ ፡ ጌታ ፤ ለጌታ ፡ እስኪ ፡ እልል ፡ በሉ
ለጌታ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፤ ለጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ቢሰዋ
ለጌታ ፡ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ፡ አዳኝ ፡ ነውና