ከእንግዲህማ (Kengedihema) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 1.jpg


(1)

ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው
(Nuroyie Bekidan New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ፡ ነበር
ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ
ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን ፡ አንስቼ
የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው (፪x)

ያሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ ያን ፡ የትላንቱን (፫x)
አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያን ፡ ሃይሉን ፡ ሳምን (፫x)
በእውነት ፡ ላመልከው ፡ ከልቤ ፡ ስነሳ (፫x)
ሁሉን ፡ አሳመረው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፫x)

አዝ፦ ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ
ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ
ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም
ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፤ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፤ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና
(፪x)

ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ፡ ነበር
ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ
ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን ፡ አንስቼ
የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው

የቆመው ፡ ተራራ ፡ ፊቴ ፡ ተከምሮ (፪x)
አይመስልም ፡ ሚታለፍ ፡ እንደሚከብድ ፡ ሆኖ (፪x)
ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ለአምላኬ ፡ መቼ ፡ አስቸገረው (፪x)
በተአምራቱ ፡ ሁሉን ፡ ሜዳ ፡ አደረገው (፪x)

አዝ፦ ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ
ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ
ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም
ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፤ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፤ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና
(፬x)