እግዚአብሔር ፡ ይነሳል (Egziabhier Yenesal) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 1.jpg


(1)

ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው
(Nuroyie Bekidan New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

እግዚአብሔር ፡ ይነሳል ፡ ክብሩን ፡ ይመልሳል
እኔ ፡ እምቢ ፡ ብል ፡ እንኳን ፡ ትውልድን ፡ ያስነሳል
ጌታዬ ፡ ይነሳል ፡ ክብሩን ፡ ይመልሳል
እኔ ፡ እምቢ ፡ እንኳን ፡ ያናውን ፡ ያስነሳል

ፍቅር ፡ ተለማምዶ ፡ ምህረት ፡ የሚያወራ
አንተን ፡ አሳዝኖ ፡ ምንም ፡ የማይፈራ
ሲታይ ፡ መልአክ ፡ ነው ፡ ውስጡ ፡ የፈረሰ
ሊታደስ ፡ ይችላል ፡ ሃይልህ ፡ ከፈሰሰ

አዝ፦ አንዴ ፡ ጠብቀን ፡ እድልን ፡ ስጠን
እንመለሳለን ፡ እጅህ ፡ ሳትመታን

አንዱ ፡ ከአንዱ ፡ ጋራ ፡ የታለ ፡ ፍቅር
መያያዙን ፡ ትቶ ፡ ወሬ ፡ ሲቆፍር
አንድነት ፡ የለውም ፡ ተነካክሶ ፡ አለቀ
ይሄ ፡ ክፉ ፡ መዘዝ ፡ ለሌላም ፡ ዘለቀ

አዝ፦ አንዴ ፡ ጠብቀን ፡ እድልን ፡ ስጠን
እንመለሳለን ፡ እጅህ ፡ ሳትመታን

መለክት ፡ አለኝ ፡ ብሎ ፡ ከቃልህ ፡ የወጣ
ከአንተ ፡ አስመስሎ ፡ ከራሱ ፡ ያመጣ
በስሜት ፡ ተገፍቶ ፡ ህዝቡን ፡ እያመሰ
በዚህ ፡ ነገር ፡ እንኳን ፡ ስንቱ ፡ አለቀሰ

አዝ፦ አንዴ ፡ ጠብቀን ፡ እድልን ፡ ስጠን
እንመለሳለን ፡ እጅህ ፡ ሳትመታን

በዕውቀት ፡ ተወጥሮ ፡ መስሎት ፡ የአደገ
ለስተቱ ፡ ሁሉ ፡ ጥቅስ ፡ እየፈለገ
ያለ ፡ እየመሰለው ፡ ጠፋ ፡ ይሄ ፡ ስዉ
ማወቅ ፡ መች ፡ ጠቀመው ፡ ሕይወት ፡ ከሌለው

አዝ፦ አንዴ ፡ ጠብቀን ፡ እድልን ፡ ስጠን
እንመለሳለን ፡ እጅህ ፡ ሳትመታን
እግዚአብሔር ፡ ይነሳል ፡ ክብሩን ፡ ይመልሳል
እኔ ፡ እምቢ ፡ ብል ፡ እንኳን ፡ ትውልድን ፡ ያስነሳል

ይሄ ፡ ለጥቅሙ ፡ ያኛውን ፡ ሲገፋ
ራሱን ፡ ለማሳየት ፡ መለከት ፡ ሲያስነፋ
የአንተን ፡ ተወት ፡ አድርጐ ፡ ለእራሱ ፡ ሲጥር
ክብርህን ፡ ተጋፍተውን ፡ ጠፍተን ፡ እንዳንቀር

ሕይወትን ፡ ሰጥተኸው ፡ ከእጅህ ፡ ላይ ፡ በልቶ
እንዴት ፡ ነው ፡ ሚለየው ፡ ሄዶ ፡ ተቀይጦ
ስምህን ፡ ግን ፡ ይዟል ፡ ተግባሩ ፡ ግን ፡ ሌላ
እየተዘናጋን ፡ ጽዋህ ፡ እንዳትሞላ

አዝ፦ አንዴ ፡ ጠብቀን ፡ እድልን ፡ ስጠን
እንመለሳለን ፡ እጅህ ፡ ሳትመታን
እስቲ ፡ ጠብቀን ፡ ትንሽ ፡ ታገሰን
እንመለሳለን ፡ ሳታዋርደን