From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የውስጤ ፡ የእኔ ፡ ፍላጐቴ
ክብርህ ፡ ነው ፡ የሁሌ ፡ ጥማቴ
ለሃገር ፡ ለወገን ፡ መፍትሄ ፡ ስንሆን
የተወሰድብን ፡ ሲመለስልን
ይሄ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ የውስጤ ፡ ርሃቤ
ይህንን ፡ አያለሁ ፡ አምኖሃል ፡ ልቤ
የቤትህ ፡ ስርአት ፡ ተበላሽቶ
ተው ፡ የሚል ፡ የሚመልሰን ፡ ጠፍቶ
ይህ ፡ ሁሉ ፡ አካሄድ ፡ ያቆምና
አያለሁ ፡ ታድሶ ፡ እንደገና
አዝ፦ አያለሁ ፡ ክብርህ ፡ ቤትህን ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ያዘነው ፡ ተጽናንቶ
አያለሁ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር
አያለሁ ፡ ታድሶ ፡ በክብር
አያለሁ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲገረም
አያለሁ ፡ ትንቢቱም ፡ ሲፈጸም
ከጥንቱ ፡ የነበረው ፡ ሃይልህ
ለትውልድ ፡ መፍትሄ ፡ የነበርህ
አያለሁ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ሲያበራ
በእጥፍ ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ሲሰራ
አዝ፦ አያለሁ ፡ ክብርህ ፡ ቤትህን ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ያዘነው ፡ ተጽናንቶ
አያለሁ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር
አያለሁ ፡ ታድሶ ፡ በክብር
አያለሁ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲገረም
አያለሁ ፡ ትንቢቱም ፡ ሲፈጸም
ሕይወቱ ፡ ኑሮው ፡ የጨላለመ
በሃዘን ፡ ልቡ ፡ የደካከመ
አያለሁ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ሲመጣ
ጥያቄ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ሲፈታ
አዝ፦ አያለሁ ፡ ክብርህ ፡ ቤትህን ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ያዘነው ፡ ተጽናንቶ
አያለሁ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር
አያለሁ ፡ ታድሶ ፡ በክብር
አያለሁ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲገረም
አያለሁ ፡ ትንቢቱም ፡ ሲፈጸም
|