From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ሰማዩ ፡ ጸጥ ፡ አለ ፡ ያ ፡ ዝናቡ ፡ ጠፋ
ዳመናም ፡ አይታይ ፡ ምንም ፡ አያካፋ
ምድርም ፡ ጸጥ ፡ አለች ፡ መሬቱም ፡ ደረቀች
ለምልሞ ፡ የነበረው ፡ ጠውልጐ ፡ አለቀ
ሰው ፡ ገሸሽ ፡ አለ ፡ ከቀኝ ፡ ከግራዬ
ተስፋ ፡ ቢስ ፡ አደረጉኝ ፡ በዝቶ ፡ መከራዬ
አሁን ፡ ተሳሳቱ ፡ መች ፡ እንዲህ ፡ ልቀር
በጊዜው ፡ ይመጣል ፡ ተስፋ ፡ የእግዚአብሔር
አዝ፦ ሰማይ ፡ ጸጥ ፡ ቢል ፡ ዝናብ ፡ ባይዘንብ
ምድርም ፡ ደርቃ ፡ ብትጠወልግ (አምንሃለሁ)
ደማናም ፡ ሳይኖር ፡ ዝናብ ፡ ይዘንባል
ባዶ ፡ ሸለቆ ፡ ውኃ ፡ ይሞላል (አምንሃለሁ)
ዘመድ ፡ አዝማዴ ፡ ከእኔ ፡ ቢርቅ
ንብረቴ ፡ ያልኩት ፡ ተወስዶ ፡ ቢያልቅ (አምንሃለሁ)
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የፍጥረት ፡ ጌታ
ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ያመኑህ ፡ ለታ (አምንሃለሁ)
አብርሃም ፡ አረጀ ፡ ሳራም ፡ ያው ፡ ደከመች
ዕድሜያቸው ፡ አበቃ ፡ ልጅ ፡ የሚስሙበት
የአብራሃም ፡ መድከው ፡ ጌታን ፡ መች ፡ ቸገረው
ያዛሬ ፡ አመት ፡ ልጅን ፡ ትወልዳለህ ፡ አለው
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ ብለው ፡ ተሳሳቁ
የማይሆን ፡ መስሏቸው ፡ ያለውን ፡ ሳያውቁ
በእርግጥም ፡ ይመስላል ፡ከሚታየው ፡ ነገር
አንተ ፡ እመን ፡ እንጂ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለእግዚአብሔር
አዝ፦ ነገሬ ፡ ቢቆይ ፡ ቢዘገይ ፡ እንኳን
የምፈልገው ፡ አሁን ፡ ባይመጣም (አምንሃለሁ)
የማየው ፡ ነገር ፡ ግራ ፡ ቢያጋባኝ
ያልከውን ፡ እንጂ ፡ አልሰማም ፡ ሌላ (አምንሃለሁ)
እንደሰው ፡ መቼ ፡ ቃልህ ፡ ይዞራል
ለሚያምኑህ ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ ሆነሃል (አምንሃለሁ)
አንተ ፡ ተናግረህ ፡ ማይሆን ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉን ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ ታደርጋለህ (አምንሃለሁ)
ጻድቅ ፡ ሰው ፡ ነበር ፡ እዮብ ፡ የተባለ
እጅግ ፡ ባለፀጋ ፡ የተደላደለ
ግን ፡ ድንገት ፡ ያሃብቱ ፡ ንብረቱ ፡ ወደቀ
ሰይታን ፡ ሊፈትነው ፡ በብዙ ፡ ደከመ
ሚስቱም ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሰድበህ ፡ ሙት ፡ አለችው
የነበራት ፡ ሁሉ ፡ ጠፍቶ ፡ ስላየቺው
አንቺ ፡ ሰነፍ ፡ ብሎ ፡ ተቆጣ ፡ ይህ ፡ ጀግና
እግዚአብሔር ፡ አምኖ ፡ ሊሞት ፡ ወሰነና
ግን ፡ መቼ ፡ እንደዚህ ፡ ሕይወቱ ፡ አለፈ
በፊት ፡ ከነበረው ፡ አምሮበት ፡ አረፈ
አዝ፦ ሃብቴ ፡ ንብረቴ ፡ ከእኔ ፡ ነበረ
ድንገት ፡ ከእጄ ፡ ሁሉም ፡ በረረ (አምንሃለሁ)
ምንም ፡ ባይኖረኝ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ
መከራዎቼን ፡ በአንተ ፡ አልፋለሁ (አምንሃለሁ)
ይህ ፡ ሰውነቴ ፡ ቢዝል ፡ ቢደክም
በሽታ ፡ በእኔ ፡ ቢፈራረቅም (አምንሃለሁ)
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ አባት
አንተን ፡ አምኜስ ፡ ልሞት (አምንሃለሁ)
እመን ፡ ወንድሜ ፡ ታመን ፡ በእግዚአብሔር
አትሞኝ ፡ ጌታን ፡ አትገምተው ፡ በቀላል ፡ ነገረ
እመኜ ፡ እህቴ ፡ ታመኜ ፡ በእግዚአብሔር
አትሞኝ ፡ ጌታን ፡ አትገምቼው ፡ በቀላል ፡ ነገረ
እመን ፡ ወገኔ ፡ ታመን ፡ በእግዚአብሔር
አትሞኝ ፡ ጌታን ፡ አትጠርጥረው ፡ በቀላል ፡ ነገር
እመን ፡ ልቤ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩ ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ የፈጠረው
እመን ፡ ልቤ ፡ የተናገረው ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ የሚያደርገው
እመን ፡ ልቤ ፡ ተስፋ ፡ ቢዘገይ ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ ባይነጋም ፡ ሌቱ
እመን ፡ ልቤ ፡ አስታውስ ፡ አንጂ ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ አምነው ፡ የሞቱ
እመን ፡ ልቤ ፡ መቼ ፡ ከሰሩ ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ የታመኑ
እመን ፡ ልቤ ፡ በእምነታቸው ፤ እመን ፡ ልቤ ፡ ድልን ፡ አገኙ
|